Translation is not possible.

የመልካም ሚስት መገለጫዎች

፡ በንግግሯ፣ በአኳኋኗ፣ በእይታዋ፣ በቅርጹዋና በልብሷ በባሏ አዕምሮ ውስጥ ደስታን የምታሰርጽ ነች ፤ ያለምንም ኩራት እርሱን ትታዘዛለች ፤ ትእዛዙን ለመተግበር እራሷን ታዘጋጃለች ፡፡ የሚከተለውን የነብዩንﷺሐዲስ ማስተዋል ይገባል፡-فعن أبي هريرة رضي هللا عنه قيل لرسول هللا صلى هللا عليه وسلم أي النساء خي ر قال\" : التي تسره إذا نظر ، وتطيعه إذا أمر ، و ال تخالفه في نفسها ومالها بما يكره\" አቡሁረይራ 4 ባስተላለፉት ሐዲስ፡ ለረሡልﷺ“መልካሟ ሴት የትኛዋ ነች?”

የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፤“ሲመለከታት የምታስደስት፤ ሲያዛት የምትታዘዝ፤ በነፍሷም ይሁን በገንዘቧ በሚጠላው ነገር የማትቃረነው፡፡”ነሳኢይ፡ አህመድ፡ አልባኒ ፊሶሂህ፡ በጣም የሚያሳዝነው አብዛኞቹ ሴቶች ለሆነ ጉዳይ ከቤት ሲወጡ ተኳኩለው፣ ዘንጠውና አምረው ይወጣሉ ፤ ባሎቻቸው ከስራ ቆይተው ወደ ቤት ሲመለሱ ከሚስቶቻቸው ላይ የሚያስተውሉት ደግሞ የቆሸሸ ልብስ ፤ መጥፎ ጠረን እና የተንጨፈረረ ጸጉር ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ፍላጎቱ ይቆረጣል ፤ ይህን ባህሪ ይዛ እንዴት ባሏ ይፈልጋታል? የባሏን ፍላጎት እንዴት ታሳካለች? በመካከላቸው ፍቅር እንዴትስ ሊመጣ ይችላል?

وجاء في\" صحيح مسلم \"من حديث جابر رضي هللا عنه قال :\" إذا قدم أحدكم لي ال ف ال يأتين أهله طروقا \"يعني ال يفاجئهم في الليل ، لماذ؟ قال\" :حتى تستحد المغي بة وتمتشط الشعثة \" ، ሙስሊም

በዘገቡት ጃቢር የሚከተለውን

አስተላልፈዋል፡-“አንዳችሁ (ሰፈር ቆይቶ ወደ አገሩ) ሲገባ (ቀድሞ ለቤተሰብ ሳይናገር) ድንገት በሌሊት ወደቤተሰቦቹ አይግባ፡፡” ለዚህ የሰጡት ምክንያት የሚከተለው ነው፡- “ባሏ ለብዙ ጊዜ ተለይቷት የቆየች ሴት ያደጉ ጸጉሮችን እንድትላጭ ፤ የተንጨፈረረ ጸጉሯን በደንብ እንድታበጥር ነው፡፡”

Send as a message
Share on my page
Share in the group