Translation is not possible.

እንዲህም ይለናል፦

«وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ .»

«ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰዉ፣ ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለዉም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎች ነዉ። »

[ኣሊ ዒምራን: 85]

°

እንዲህም ይለናል፦

«وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا»

«ቅኑም መንገድ ለርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእመኖቹ መንገድ ሌላ የሆነን የሚከተል ሰው፣ (ከዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን (በመረጠው ላይ እንሾመዋለን!)፤ ገሀነምንም እናስገባዋለን፤ መመለሻይቱም ከፋች‼»

[አን-ኒሳእ: 115]

ለእኛ የተመረጠልንና የተወደደልን እውነተኛ የሆነ ሁለንተናዊ ሙሉዕ እምነት እስልምና መሆኑን እንዲህ ሲል ይነግረናል፦

«الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا ۚ »

«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ።»

[አል-ማኢዳህ: 3]

ይህን ዲን ትተህ ምን ፍለጋ ነው ኢሬቻ የምትወጣው?!

📌 አላህ የፈጠረን እርሱን እንድናመልክ እንጂ ዋቃን እንድናመልክ አይደለም።

አላህ እንዲህ ይለናል፦

«وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ .፝

«ጋኔንንና ሰውን ሊገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።፝

[አዝ-ዛሪያት: 56]

እርሱን ማምለክ እንጂ ሌላን እንዳናጋራ ነግሮናል።

«وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ »

«አላህን ተገዙ፤ በርሱም ምንንም አታጋሩ።»

[አን-ኒሳእ: 36]

«يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩»

« እናንተ ያመናችሁ ስዎች ሆይ (በስግደታችሁ) አጎንብሱ፣ በግንባራችሁም ተደፉ፣ ጌታችሁንም ተገዙ፤ በጎንም ነገር ሥሩ፤ ልትድኑ ይከጃልላችኋልና።»

[አል-ሐጅ: 77]

°

«وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ حُنَفَاءَ وَيُقِيمُوا الصَّلَاةَ وَيُؤْتُوا الزَّكَاةَ ۚ وَذَٰلِكَ دِينُ الْقَيِّمَةِ»

«አላህን፣ ኃይማኖትን ለርሱ ብቻ አጥሪዎች ቀጥተኞች ኾነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፣ ዘካንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲኾኑ (ተለያዩ)። ይህም የቀጥተኛዪቱ (ኃይማኖት) ድንጋጌ ነው።»

[አል-በዪይናህ: 5]

«فَادْعُوا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ»

«አላህንም ከሐዲዎች ቢጠሉም ኃይማኖትን ለርሱ አጥሪዎች ሆናችሁ ተገዙት።»

[አል-ጛፊር: 14]

*

አላህ የተከበሩና እጅጉን የተዋቡ መልካም ስሞችና መገለጫዎች አሉት።

\"ዋቃ\" የሚባል ስያሜ ግን የለውም።

ስለዚህ ስለምንም ሆነ ስናመሰግን \"ዋቃ!\" የሚለውን አንጠቀምም።

አላህ አንዲህ ይለናል፦

«وَلِلَّهِ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ فَادْعُوهُ بِهَا ۖ وَذَرُوا الَّذِينَ يُلْحِدُونَ فِي أَسْمَائِهِ ۚ سَيُجْزَوْنَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ »

«ለአላህም መልካም ስሞች አሉት፤ (ስትጸልዩ) በርሷም ጥሩት እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተውዋቸው፤ ይሠሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ።»

[አል-አዕራፍ: 180]

*

«

هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ »

«እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።»

[አል-ሐሽር: 24]

*

«فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ »

«…ለርሱ መልካም ስሞች አሉትና…»

[አል-ኢስራእ: 110]

||

👉 አንዳንድ ሙስሊሞች ደግሞ፤

«እኛ የምንሄደው በበዓሉ አምነንበት ልናመልክ ሳይሆን፤

የብሄራችንን አንድነት ያመጣ ስለሆነ ማክበር አለብን!» ሲሉ ይደመጣሉ።

ለእነዚህ ሙስሊሞች የምላቸው ነገር፤

ምንም እንኳ በዓሉን የብሄራቸው መገለጫ ወይም መለያ የሆነ ወግና ባህል አድርገው ቢያስቡትም፤

ዋቃ የተሰኘ ሌላ አምላክ ከአላህ ውጭ ተጠርቶ ወደሚመለክበት ቦታ ህዝቡን «አታክብሩ!» ብሎ ለማስተማር አላማ ካልሆነ በስተቀር እግራቸው ማቅናት እንደሌለበት ነው።

ከመሠረታዊ ዲን ጋር የሚቃረን ባህልም ይሁን እሴት ጉድጓድ ውስጥ ሊጨመር ይገባል።

ቀደምት የአላህ ደጋግ ባሮች (ሰለፎች) እንኳን አላህ የሚታመጽበትን ቦታ ሊታደሙ፤

ትንሽ መጥፎ ነገር ሲመለከቱ እንኳ ላለማዬት አይናቸውን ይሸፍኑ ነበር።

አላህ ትክክለኛ አማኞችን እንዲህ ነበር የገለጻቸው፦

« وَالَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ الزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا بِاللَّغْوِ مَرُّوا كِرَامًا»

«እነዚያም፣ እብለትን የማይመሰክሩ፤ በውድቅ ቃልም (ተናጋሪ አጠገብ) ባለፉ ጊዜ፣ የከበሩ ሆነው የሚያልፉት ናቸው።»

[አል-ፉርቃን: 72]

ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን በዓል አለመጣድ (አለማክበር) ነው ብለዋል ኢብኑ ዐብ-ባስ።

ስለዚህ እንደት ሌላ አምላክ ወደሚመለክበት ቦታ ይኬዳል?!

እንዳውም የቻለ ሊከለክል ይገባል እንጂ።

||

በአጠቃላይ፦

✔ የኢሬቻ በዓል ከእስልምናችን ጋር በጣም ይጋጫል።

✔ ማንኛውም ሙስሊም የሆነ ሰው ወደዚህ ቦታ ከመሄድ ሊቆጠብ ይገባል።

✔ ወላጆች አላህን ፍሩና ልጆቻችሁን ልታስተምሩና ልትከለክሉ ይገባል።

✔ዳዒዎች በተለይም የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የሆናችሁና ኦሮምኛ ቋንቋ የምትችሉ እንዲሁም በህዝቡ ዘንድ አንፃራዊ ተቀባይነተና ተሰሚነት ያላችሁ ግለሰቦች፤

እባካችሁ ህዝቡ ሺርክ ላይ ሲታደም እያያችሁ ዝም አትበሉ።

«እኛ አክብሩ አላልን!» ወዘተ እያላችሁ አትሞግቱ።

ሲያጠፉ አይቶ ዝም ማለትም ያስጠይቃልና።

በምትችሉት ነገር ሁሉ ህዝቡን ታደጉት።

የኦሮሚያ ህዝብ አብዛሃኛው ሙስሊም ይሁን እንጂ፤

በብዙ እሴቶቹ ግን የገዳው ስርኣትንና የዋቄፈናን አንዳንድ ነገሮች እንደ እምነት አስቦ ሳይሆን እንደ ባህል ወስዶ ሲፈጽማቸው ይስዋላል፣ ይህ ስህተት ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group