Translation is not possible.

የኢሬቻ በዓልን በተመለከተ‼

===================

«ስለ በዓሉ በማስተማር፤ ወደ ሺርክ እየተመመ ያለውን ሙስሊም ማህበረሰብ ፈጥነን እንታደግ‼»

✍ የኢሬቻ በዓል በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ተወላጆች ዘንድ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ሲዳማና አካባቢዋ ነዋሪዎች ዘንድ በስፋት ይከበራል። \"ኢሬቻ\" ለኦሮሚያ ክልል ተወላጆች አንድነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ይነገራል።

\"ለመሆኑ ኢሬቻ ምንድን ነው?\" የሚለውን ጽንሰ ሃሳብና ከጉዳዩ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን አንዳንድ ነጥቦች እንመልከት።

↓↑

👉 «ኢሬቻ» ማለት በቃል ደረጃ «ምስጋና» ወይም «አምልኮ» እንደማለት ነው።

ይህ ምስጋና የሚቀረበው አምላክ ተብሎ ለሚታሰበው ለዋቃ ጉረቻ (Waaqaa Gurracha) ነው።

«ዋቃ ጉረቻ» ማለት «ጥቁር አምላክ» እንደማለት ነው። ምክንያቱም የዚህ እምነት ተከታዮች \"ዋቃን (አምላክን)\" «ጥቁር ነው!» ብለው ያስቡታል።

አጠቃላይ የእምነቱ ስያሜ፤

«ዋቃ (አምላክ) [Waaqaa]» ከሚለው ስርወ ቃል የተወሰደ ሲሆን «ዋቄፈና (Waaqeffannaa)» ይባላል።

ለዋቃ ጉረቻ ምስጋና አቅራቢ የሆኑት የዚህ የዋቄፈና እምነት ወንድ አማኞች «ዋቄፈታ (Waaqeffattaa)» ይሰኛሉ።

ሴት አማኞቹ ደግሞ «ዋቄፈቱ (Waaqeffattuu)» ተብለው ይጠራሉ።

ይህ እምነት በመመሪያነት የያዘው የተጠናቀረ ኃይማኖታዊ መጽሐፍም ሆነ የተጣራ ሌላ መመሪያ የለውም።

እምነቱ በባህላዊ መንገድ የተያዘ ዘልማዳዊ ነው።

°

✅ የዋቄፈና እምነት ተከታዮች፤

ክረምቱ ሲነጋ፤ ውሃ ሙላቱ አልቆ አደይ ሲፈነዳ፣ በውሃ ሙላት ተራርቆ የነበረው ህዝብ ውሃው ጎሎለት ወንዙን አቋርጦ ሲገናኝና ሲጠያየቅ፣ ደፍርሶ የነበረው ውሃ ሲጠራ መስከረም አጋማሽ አካባቢ ላይ ለዋቃ ለአምላካቸው ምስጋና ያቀርባሉ።

ምስጋና የማቅረብ አምልኳቸውን የሚፈጽሙት እርጥብ ሣር (ጨሌ) እና አደይ አበባ በመያዝ በዛፎች፣ በወንዞች ዳርቻ፣ በተራራዎችና በመሳሰሉት ነው።

√ ለኦዳ ዛፍ ልዩ ክብር አላቸው።

በዛፉ ስርም ያርዳሉ፣ ሌሎች አምልኮዎችንም ይፈጽማሉ።

የዛፏን ምስል አሰርተው አንገታቸው ላይ የሚያንጠለጥሉም አሉ።

`

የያዙትን እርጥብ ሣር ከወንዙ ውሃ ውስጥ ነክረው በማውጣት የውሃውን መጥራት ያስተውላሉ።

አምልኳቸው (ምስጋናቸው) በወንዞች ዳርቻ (በሐይቆች) እና በተራሮች የሚፈጸም እንደመሆኑ መጠን፤ ወደ 7 አካባቢ የሚጠጉ ታዋቂ ሐይቆችና እንዲሁም 8 የሚሆኑ ተራሮች አሉ።

√ «ሆረ» ማለት «ሐይቅ» ማለት ሲሆን፤

ለምሳሌ፦ ሆረ ፊንፊኔ፣ ሆረ አርሰድ፣ ሆረ ኪሎሌ ወዘተ የተሰኙ የዋቃ ሐይቆች አሉ።

ከነዚህም ውስጥ ከጥንት ጀምሮ በስፋት የሚታወቀውና እስካሁን ድረስ የኢሬቻ በዓል ሲከበርበት የነበው በቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት) የሚገኘው የ«ሆረ አርሰድ» ሐይቅ ዋነኛው ነው።

በፊት የሚከበረው አዲስ አበባ ላይ ቢሆንም ከሚኒልክ በኋላ ግን ለተወሰኑ አመታት እንደተከለከለና በኋላም ወደ ደብረ ዘይት (ቢሾፍቱ) እንደተዛወረ ይነገራል።

√ «ቱሉ» ማለት ደግሞ «ተራራ» ማለት ሲሆን፤ ቱሉ ጩቋላ (የዝቋላ ተራራ)፣ ቱሉ ኤረር ወዘተ የተሰኙት አምልኮው የሚፈጸምባቸው የዋቃ ተራሮች ናቸው።

በዚህ የምስጋና ማቅረብ አምልኮ ላይ፤

ዋቄፈታዎች እርጥቡን ሳር በመያዝ ከሐይቁ እየነከሩ ዋቃ ጉረቻን በማመስገን፤ ይዘምራሉ፣ ይጨፍራሉ።

«ኢሬቻ» የምትለዋ ቃልም ይህንን ተግባር ጠቋሚ ናት።

በዚህ ወቅት አምላክ (ዋቃ) በጥቁር ደመና መልክ ተመስሎ ይመጣል ብለው ያምናሉ።

ይህን አምልኮ ፈጻሚ ምዕምናን ዋቄፈታዎች «ሚሤንሣ» ሲባሉ፤

እምነቱን የሚመሩት ካህናቶች ደግሞ «ቃሉ» ይባላሉ።

ፖለቲካውን የሚመሩት ደግሞ «ገዳ» በመባል ይታወቃሉ።

ይህ እምነት ምንም እንኳ መሠረታዊ የሆነ መለኮታዊ መጽሐፍት የሌለው ቢሆንም፤

በአንዳንድ መረጃዎች መሠረት ከነብዩል\'ሏህ ዒሳ ውልደት ከ3,000 አመታት በፊት (3,000 B.C) እንደተጀመረ ይነገራል። በጎርጎረሳውያኑ የዘመን ስሌት በ2007 በተደረገ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መሠረት፤

ከኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ወደ 3.3% የሚሆነው የዚህ ዘልማዳዊ እምነት ተከታይ ሲሆን፤ ቀስ በቀስ ግን ወደ 3% ገደማ እንዳሽቆለቆለ ይነገራል።

ቢሆንም ግን ከዜግነት ፖለቲካ በስተፊት ባለፉት አመታት በሃገራችን ተወልዶ የነበረውን የብሄር ፖለቲካ ተከትሎ፤

የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር ቀስ በቀስ ሊያሻቅብ እንደሚችል ይገመታል።

በሚያሳዝን ሁኔታ በኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ ከሚታደሙት ተሳታፉዎች ውስጥ፤

ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ቁጥር የሚሸፍኑት ሙስሊሞች መሆናቸው ነው።

በዚህም የተነሳ በተለይም የብሄርተኝነት አባዜ የተጠናወታቸው ሙስሊሞች፤

«ኢሬቻ» አንድነታችንን ያመጣልን በዓል ነው በማለት «አታክብሩ!» ሲባሉ እንኳ ለመስማት ፈቃደኛ አይደሉም።

እንዳውም «አታክብሩ!» የሚላቸው ሰው ብሄራቸውን ስለጠላ የሚመስላቸው ከንቱዎች ብዙ ናቸው።

በርግጥ የእምነታቸው ጉዳይ አሳስቧቸው ሳይሆን፤

የራሳቸው የብሄር ትርክት ስላለባቸው ብቻ የኦሮሞን ብሄርተኝነት በመጥላት ለፖለቲካ ቁማራቸው ሲሉ «አጋክብሩ!» የሚሉ የብሄር ፖለቲካ አቀንቃኞች መኖራቸው አይካድም።

ቢሆንም ግን አንድን ነገር የምንጠላው ጠላታችን ስለነገረን ሳይሆን፤

የጉዳዩን እውነተኝነት በመመዘን መሆን አለበት።

ከጥላትም ሐቅ ይገኛልና፤ ጠላት ለፈለገው አላማ ያንን ነገር ቢናገረውም፤

እኛ በስሜት ተነሳስተን በእልህ እብሪተኛ መሆን የለብንም።

በተይም እንደ ሙስሊም ሚዛናችን ኢስላማዊ ሊሆን ይገባል።

✍ እምነቱ የሚመራበት ምንም እንኳ መለኮታዊ መጽሐፍት ባይኖሩትም፤

በተለይ ከሞት በኋላ ያለውን መንፈሳዊ አለም በተመለከተ ከእስልምና፣ ከክርስትናና ከሌሎች እምነቶች ዘንድ የተኮረጀ ቅይጥ አመለካከት አለው።

እንዳውም አንዳንድ የእስልምና ጥልቅ እውቀት የሌላቸው ሙስሊሞች፤

«እነርሱም የሚያመልክት አንድ ዋቃን (አምላክን) ነው! ምን ችግር አለው፤ ስሙን ቀይረውት ነው እንጂ! አላህ ደግሞ ብዙ ስሞች አሉት! » ብለው ይሞግታሉ።

ይህ ትልቅ ስህተት ነው።

በዚህ ትውልድ ውስጥ ሁኖ፤

በቁርኣን የማይመራና ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት በነቢዩ ሙሐመድ (ሶለል\'ሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የማያምን ሙስሊም ያልሆነ አካል ሁሉ በግልፅ ስህተት ውስጥ ነው።

ስለዚህ እንዲህ አይነት እሳቤ ያለው ሙስሊም ካለ፤

ሞት መጥቶት ጌታውን በመጥፎ ፍፃሜ ከመገናኘቱ በፊት፤

ይህን የተሳሳተና ከመሠረታዊ እምነቱ ጋር የሚጣረስ እምነቱን ያስተካክል።

ብቸኛው አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ በቅዱስ ቁርኣን ላይ እንዲህ ይላል፦

« إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ۗ وَمَا اخْتَلَفَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ إِلَّا مِن بَعْدِ مَا جَاءَهُمُ الْعِلْمُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِآيَاتِ اللَّهِ فَإِنَّ اللَّهَ سَرِيعُ الْحِسَابِ »

«አላህ ዘንድ (የተወደደ) ኃይማኖት ኢስላም ብቻ ነዉ፣ እነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች በመካከላቸዉ ላለዉ ምቀኝነት እዉቀቱ ከመጣላቸዉ በኋላ እንጅ አልተለያዩም፤ በአላህም አንቀጾች የሚክድ አላህ ምርመራዉ ፈጣን ነዉ:።»

[ኣሊ ዒምራን: 19]

Send as a message
Share on my page
Share in the group