Translation is not possible.

~አንዲት ሴት አጋጣሚዋን እንዲህ ትናገራለች፤ የሆነ ጊዜ ኒቃብ መልበስ ፈለኩና ቤተሰቦቼን ሳማክራቸዉ አባቴም እናቴም ከለከሉኝ።ፍቃደኛ አልሆኑም ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ኒቃብ ለመልበስ ወስኜ ለበስኩ።ቤተሰቦቼ ኒቃቡን ሲመለከቱ ማንም ለትዳር አይጠይቅሺም፣መማር አትችይም፣መስራት አትችይም…እያሉ መጮህ ጀምሩብኝ።የ አላህ መሻት ሆነና በዛዉ ሳምንት  ዉስጥ የሆነ ወጣት ለትዳር ጠየቀኝ። ኒካህ ታሰረ።

ባሌም የሆነ ቀን እንድህ አለኝ«ታውቂያለሽ ከ9 አመታት በፊት ነበር የምወድሽ።ኒቃብ እስከምትለብሺ ነበር የምጠብቀዉ። ልክ እንደለበሽ አንቺን ለማግባት መጣሁ» አለኝ። ከአምስት አመታት ብሃላ  ቁርአን  በ10 አይነት አቀራር  አስሀፈዘኝ  በጣም አጋዤም ነበር።

||

☞አላህን ፈርቶ ትዕግስት የሚያደርግ ሁሉ አላህ የተሻለ ነገርን ይወፍቀዋል።

Send as a message
Share on my page
Share in the group