Translation is not possible.

የነገደ ሁሉ ሀብታም ይሆናል ማለት አይደለም ፣

ጂሃድ ያደረገ ሁሉ ያሸንፋል ማለት አይደለም ፣

የሰራ ሁሉ ያልፋል ማለት አይደለም፣

ይህ ከሆነ ውጤት ባለመምጣቱ መናደድ የለብህም! ያንተ ድርሻ ማንበብ፣ መስራት ፣ መትጋት ነው።ውጤት የአላህ ነው።

አላህ ጂሃድን እንኳን ግዴታ ሲያደርግ ማሸነፍን ግን ግዴታ አላደረገም።ድልን በራሱ እጅ ነው ያደረጋት! ትምህርት መውደቅ ማለት ጀሀነም መግባት ማለት አይደለም አኺ!

ራስን ማጥፋት የሚፈቀድ ቢሆን አላህን በመወንጀላችን ምክንያት ተፀፅተን ባጠፋናት ነበር።ለዱንያ ብለህ ራስህን አታጥፋ!

ሰበብ አድርሰህ እስከሆነ ድረስ አላህ ሌላ ኸይር ፈልጎልህ ይሆናል።

«ከዚህ በኋላ አላህ (ጉዳይን) ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡» (አጥጦላቅ 1)

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group