Translation is not possible.

«በደማስቀስ አንድ ሚስኪን የታክሲ ሹፌር ነበረ። በስህተት የህክምና ተማሪ የሆነን ልጅ በመኪናው አደጋ ያደርስበታል። ልጁም በዛ የመኪና አደጋ ሰበብ ህይወቱ ያልፋል።

ሼይኽ ሙሀመድ አይዋድ እና ሌሎች አሊሞች የፍርድ ቤት ዳኛ ወደሆነው የሟቹ አባት ጋር ይሄዳሉ። ለሚስኪኑ የታክሲ ሹፌር ይቅር እንዲለውና በምትኩ የደም ካሳ ክፍያ ያቀርቡለታል። አባትዬው በሚደንቅ ሁኔታ ‟ለአላህ ብዬ ይቅር ብዬዋለሁ እና በምትኩም ቁራጭ ሳንቲም አልፈለግም።  ነገ እራሴው ወደ እስር ቤት ሄጄ አስወጣዋለሁ” ብሎ መለሰ። ከዛም ለሼይኽ ሙሀመድ አይዋድ ‟ሼይኽ አይዋድ እርሶ ቤቴ መጥተው ቅር ብሏችሁ እንድትወጡ አልፈቅድም።” አላቸው! የታክሲ ሹፌሩ ይቅርታ ተደረገለት።

ከአመታት በኋላ አባትዬው ታመሙ ሰውነታቸው ፓራላይዝድ ሆነ። ቤተሰባቸው ለመጨረሻ ጉብኝት ወደ ሐረም መካ 🕋 ወሰዷቸው። በእንጨት ስትሬቸር ላይ አድርገዋቸው ጠዋፍ አስደረጓቸው። ይዘው እያዞሩት እያለ በእንባ እንዲህ ብሎ አላህን ተማፀነ ❝ጌታዬ ሆይ! ‟ሼይኽ አይዋድ የልጄን ገዳይ ይቅር እንድለው ሊጠይቀኝ እኔ ጋር መጣ እና እኔም ቅር ብሎህ ከቤቴ እንድትወጣ አላደርግህም።” አልኩት! ዛሬ ሰውነቴ ፓራላይዝድ ሆኖ እኔ ቤትህ መጥቻለሁ እና ቅር ብሎኝ እንዳልወጣ እጠይቅሃለሁ።❞ ዱአውን ሳይጨርስ ሰውነቱ መዳን ጀመረ ... ጠዋፉን ሰውነቱ ድኖ በእግሩ እየተራመደ ነበር የጨረሰው። በዛ ቀን ያዩት ሰዎች ሁሉ አነቡ!»

የበደሏችሁን ያስቀየሟችሁን ይቅር በሉ አላህ (ሱ.ወ) ተአምሮችን ያሳያችኋል።

✍️ Selehadin Mohammed

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group