Translation is not possible.

የሆኑ ሰዎችን አውቃለሁ። በመንገዳቸው ሁሉ መከራ የማያጣቸው። ፈተናን እንደመከተል ያለ የመዋተት ኑሮን የሚኖሩ። ግን ጭራሽ አያስታውቅባቸውም። ውስጣቸው እንደጉድ ሲቃጠልም አያስታውቁም… ልባቸውን የሚያረጥብ ዝናብ ከሰማየ ሰማያት ሲፈስላቸውም ማንም አያነባቸውም። እነሱን ስመለከት ነው… እጅግ በተረጋጉ ሰዎች ውስጥ በርካታ ያልተረጋጉ ነገሮችም ይኖራሉ ያልኩት። እና የሳቀ ሁሉ ደስታን የተሸከመ አይደለም። ስለዚህ ሳናገናዝብ የመጣልንን ሁሉ መናገር አይገባንም።

\"ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ\" በቀራህ 83

t.me/abdu_rheman_aman

Send as a message
Share on my page
Share in the group