Translation is not possible.

▣ ተውበት ላደረጉ አሏህ ይምራል!

۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡

📗 ቁርኣን ሱራ አዝ\'ዙመር 39:53

ታላቁ ተንታኝ ኢብኑ ከሲር ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ:-

በዚህ በተከበረችው አንቀፅ ለሁሉም አማፂያን ከከሃዲም ሌሎችንም ወደ ፀፀት (ተውበት) እና መመለስ ጥሪ አለበት እንዲሁም አሏህ ወንጀልን ሁሉ ለተፀፀተና ከእርሷ ለተመለሰ ወንጀሏ ምንም ያህል ብትሆን ምንም ያህል ብትበዛ እንደ ባህር አረፋ እንኳ ብትሆን እንደሚምር ይገልፃል።

ይህች አንቀፅ ያለ ፀፀት (ተውበት) መተርጎም ትክክል አይሆንም ምክንያቱም ከሽርክ ላልተፀፀተ ከእርሱ ይቅር አይባልምና።

📗 ተፍሲር ኢብኑ ከሲር 4/75

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا

አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡

📗 ቁርኣን ሱራ አን\'ኒሳእ 4:48

የሙፈሲሮች ኢማም አጥ\'ጠበሪይ እንዲህ አሉ:-

አሏህ በእሱ ላይ ማጋራትና መካድ ላልተፀፀተ አይምርም ከእዚህ ውጭ ላለው ለፈለገው ከወንጀልና ከሀጢአት ሰዎች ይምራል።

📗 ተፍሲር አጥ\'ጠበሪይ 4/128

ይህንን አንቀፅ በማስመልከት ኢብኑ ከሲር እንዲህ አሉ:-

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ

አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም ማለትም በእርሱ ላይ አጋሪ ሆኖ ለተገናኘው ባሪያው አይምርም።

وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ

ከዚህ ሌላ ያለውንም (ኀጢአት) ይምራል ማለትም ከወንጀሎች

لِمَن يَشَاءُ

ለሚሻው ሰው ይምራል ማለትም ከባሮቹ

📗 ተፍሲር ኢብኑ ከሲር 1/701

إِنَّمَا التَّوْبَةُ عَلَى اللَّهِ لِلَّذِينَ يَعْمَلُونَ السُّوءَ بِجَهَالَةٍ ثُمَّ يَتُوبُونَ مِن قَرِيبٍ فَأُولَٰئِكَ يَتُوبُ اللَّهُ عَلَيْهِمْ ۗ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

ጸጸትን መቀበል በአላህ ላይ የሚገባው ለእነዚያ ኀጢአትን በስህተት ለሚሠሩና ከዚያም ከቅርብ ጊዜ ለሚጸጸቱት ብቻ ነው፡፡ እነዚያንም አላህ በእነርሱ ላይ ጸጸትን ይቀበላል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

📗 ቁርኣን ሱራ አን\'ኒሳእ 4:17

https://t.me/Wku_ms_Official_Channel/

Telegram: Contact @Wku_ms_Official_Channel

Telegram: Contact @Wku_ms_Official_Channel

ይህ ቻናል ትክክለኛው የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሲሆን፣ በቻናሉም፦ ➲ ሙስሊም ተማሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎች ➲ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መስጂድ ስለሚደረጉ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎች ለምሳሌ ➩ የዳዕዋ ፕሮግራም ➪ የቂርአት እንቅስቃሴ ➪ ሌሎችም ዝግጅቶች ሲኖሩ የሚለቀቁ ይሆናል በአላህ ፍቃድ። @Wku_ibnuabbas_bot https://t.me/Wku_ms_Official_Channe
Send as a message
Share on my page
Share in the group