Translation is not possible.

☞የአሹራ ፃም ደረጃዎች

☞ይበልጥ የተወደደው የአሹራ አፃፃም

«ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።»

📝የአሹራ ፃም አራት ደረጃዎች አሉት።

√ የመጀመርያውና ዋናው ደረጃ

« ይህም የሚሆነው ዘጠነኛው፣ አስረኛውና አስራ አንደኛው ቀን መፃም ነው።

☞ እነዚህ ሶስት ቀናቶች በተከታታይ መፃም ከሁሉም የተሻለና ትልቁ ደረጃም ነው። በዚህ ላይ የሚጠቁም መረጃ መቷል። ኢማሙ አህመድ ሙስነዳቸው ላይ እንዳሰፈረቱ የአላህ መልእክተኛ (ከአሹራ በፊትና በኋላ በመፃም አይሁዶችን ተቃረኗቸው) ብለዋል።

⁍አንድ ሰው እነዚህን ቀናቶች ከፃመ በየወሩ ሶስት ቀን መፃም የሚያስገኘውን ትልቅ ትሩፋትንም ያገኛል።

√ ሁለተኛው ደረጃ

ይህም ዘጠነኛውና አስረኛውን ቀን መፃም ነው።

የአላህ መልእክተኛም ይህን አስመልክቶ አይሁዶች አስረኛውን ቀን ብቻ ነው የሚፃሙት ሲባሉ፦ አይሁዶችን መፃረር ይወዱ ነበርና {ቀጣይ አመት አላህ ካኖረን ዘጠነኛውንም ጨምረን እንፃማለን ብለው ነበርና}። ይህ ማድረግ ደሞ ሁሉንም ካፊሮች መፃረርም ጭምር ነው።

√ ሶስተኛው ደረጃ

⁍ አስረኛውና አስራ አንደኛው ቀን መፃም ነው።

√ አራተኛውና የመጨረሻው ደረጃ

☞ይህም አስረኛውን ቀን ብቻ መፃም ነው።

«ስረኛውን ቀን ብቻ ነጥሎ መፃም በተመለከተ ከፊል ኡለማዎች የተፈቀደ ነው ሲሉ ከፊሎቹ ደሞ የተጠላ ነው ብለዋል።»

👉ከመረጃ አንፃር ይጠላል የሚለው ጠንካራ ስለሆነ ከዚህ ጭቅጭቅ ለመውጣት ሲባል ከአሹራው ቀን በፊት አንድ ቀን ማስቀደም ወይም ከአሹራ ቀን በኋላ አንድ ቀን ማስከተል ያስፈልጋል።

[سلسلة لقاء الباب المفتوح (٩٥)]

∽ማሳሰቢያ‼️

〰〰〰〰〰

አንዳንድ ኡለማዎች አስረኛውን ቀን ብቻውን መፃም ይጠላል ማለታቸው፦ ፃሙ ተቀባይነት የለውም ወይም ውድቅ ነው ማለት እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል።

=

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Telegram: Contact @Sadik_Ibnu_Heyru

Telegram: Contact @Sadik_Ibnu_Heyru

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ➲የአቂዳ ኪታቦች ➲የፊቅህ ግንዛቤዎች ➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ ➲ወቅታዊ ምክሮች ➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Send as a message
Share on my page
Share in the group