#በወንጀል_ቅጣት_ምልጃ_መከልከሉ
አላህ እንዲህ ብሏል፦
\"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለት እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ እንደኾነ) መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ። በአላህና በመጨረሻ ቀን የምታምኑ እንደኾናችሁ (አትፍሩ)።\" (አንኑር፡ 2)
#ሐዲሥ 350 / 1770
ዓኢሻ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ ቁረይሾች የስርቆት ወንጀል የፈጸመች የመኸዙሚይያህ ጎሣ አባል የሆነች እንስት ጉዳይ አሳሰባቸው። \"በርሷን ጉዳይ የአላህን መልዕክተኛ የሚያናግራቸው ማን ነው?\" ተባባሉ። \"የአላህ ወዳጅ የሆነው የዘይድ ልጅ እንጅ ሌላ ማንም ደፍሮ አያናግራቸውም\" ሲሉም ወሰኑ። ኡሳማ የአላህን መልዕክተኛ አናገራቸው፦ \"የአላህን ቅጣት ውሳኔ ለማስቀረት አማላጅ ሆነህ ትመጣለህን?\" ሲሉ ገሰጹት። ከዚያም ቆሙና እንዲህ በማለት ተናገሩ፦ \"ከእናንተ በፊት የነበሩ ሕዝቦችን ያጠፋው ከመካከላቸው የተከበረ ወገን የሆነ ሰው በሰረቀ ጊዜ ይተውታል። ደካማው በሰረቀ ጊዜ ግን የወንጀል ቅጣት ተፈጻሚ ያደርጉበታል። በአላህ እምላለሁ! የሙሐመድ ልጅ ፋጢማ ብትሰርቅ እንኳ እንጇን ከመቁረጥ ወደኋላ አልልም።\" (ቡኻሪና ሙስሊም)
በሌላ ዘገባ እንደተወሳው፦ መልዕክተኛ የኡሳማን ምልጃ ሲሰሙ ፊታቸው ተለዋውጦ፦ \"የአላህን የቅጣት ውሳኔ ተፈጻሚነት ለማስቀረት አማላጅ ሆነህ ትመጣለህን?\" ሲሉ ገሰጹት። ኡሳማም፦ \"የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ከአላህ ምሕረት ይለምኑልኝ?\" አላቸው። በመጨረሻም የሌባዋ እጅ እንዲቆረጥ አዘዙ። ተቆረጠ።
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ ሸሪዓዊ የቅጣት ውሳኔን በምልጃ ለማስቀረት መሞከር ክልክል ነው። የፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈጻሚ መሆን አለበት።
2/ ሕግ ለሁሉም በእኩል ደረጃ ያለ አድሎ መሥራት አለበት። ሁሉም ከሕግ ፊት እኩል መሆን አለበት። ከሕግ በላይ የሆነ አካል መኖር የለበትም።
3/ ፍትትህ ማዛባት ለሕዝቦች መበስበስ፣ መውደቅና መንኮታኮት ምክንያት ሊሆን ይችላል።
4/ ሐዲሡ የኡሳማ ኢብኑ ዘይድን ልቅናና ከነቢዩ ዘንድ የነበረውን ቀረቤታ ያሳያል።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1