Translation is not possible.
#ወደ_መቃብር_ዞሮ #መስገድ_ስለመከልከሉ
#ሐዲሥ 342 / 1757
የአላህ መልዕክተኛ ተከታዩን ሲናገሩ ሰምቻለሁ በማለት አቢ መርሠድ ከንናዝ ኢብኑ አልሑሶይን አስተላልፈዋል፦ "ወደ መቃብር ዞራችሁ አትስገዱ። በርሷም ላይ አትቀመጡ።" (ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ ወደ መቃብር ዞሮ መስገድ እሷን ከፊት ለፊት ለማድረግ አስቦ ካደረገው ክልክል ነው። ይህን ሳያስብ ወደርሱ ዞሮ ከሰገደ እና በርሷና በቀብሩ መካከል የሚጋርድ ነገር ከሌለ ይጠላበታል። የሚጋርድ ነገር ግን አይጠላም።
2/ ይህ ነጥብ ይህን ያህል ክብደት የተሰጠው ከአላህ ውጭ የሆነን አካል የማላቅ "ፊትና" እንዳይከሰት ለመከላከል ነው።
3/ ቀብር ላይ መቀመጥም እንዲሁ ተከልከሏል። አላህ ያከበረውን የሰውን ልጅ ደረጃ ዝቅ ማድረግ በመሆኑ።
Umma Life
https://ummalife.com/MuslimEthio
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group