Translation is not possible.

#ሶላት_ውስጥ #ያለ_ምክንያት_መዟዟር_ስለመጠላቱ

#ሐዲሥ 341 / 1755

ዓኢሻ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ ሶላት ውስጥ ስለመዘዋወር ጠይቄያቸው፦ “እርሱ ሰይጣን የሚፈጽመው ጠለፋ ነው” በማለት መለሱልኝ። (ቡኻሪ)

#ሐዲሥ 341 / 1756

አነስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ “ሶላት ውስጥ መዟዟር ጥፋት ነውና። መዟዟርህ የግድ ከሆነ በሱንና እንጅ በግዴታ ሶላቶች መሆን የለበትም።” (ቲርሚዚ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ሶላት ውስጥ መዟዟር ይጠላል። ልቦና ከሶላት መዘናጋቱንና በሌላ ነገር ጠመዱን ያመለክታል። ለዚህም ነው ሰይጣን የሚፈጽመው ጠለፋ ነው የተባለው። ሰይጣን የሰጋጁን መዘናጋት ተጠቅሞ ስሜቱን ይሰርቀዋል። ወደ ሌላ አቅጣጫም ያዞረዋል።

2/ ሶላት ውስጥ መዟዟር ጥፋት ነውም ተብሏል። ዒባዳ ውስጥ አላህን ትቶ ለሰይጣን ጉትጎታ ጆሮ መስጠት በመሆኑ። በተጨማሪም የሚጠሉ ነገሮችን ማቃለልና ደጋግሞ መፈጸም ሐራም ላይ ሊጥል ይችላል። ለቅጣትም ያበቃል።

3/ መዟዟር ለአንዳች ምክንያት ወይም ችግር ከሆነ ግን አይጠላም።

4/ እስካሁን የተጠቀሰው ፊትን ብቻ ማዞርን በተመለከተ ነው። ደረትን ማዞር ግን ሐራም ነው። ሶላትንም ያበላሻል። ምክንያቱም ከሶላት መሠረታዊ መስፈርቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ወደ ቂብላ የመዞርን መስፈርት ስለሚያጠፋ ነው።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group