Translation is not possible.

♻️ 🔻 እስራኤል የራፋህ ዘመቻዋን እንድታቆም ፍርድ ቤቱ አዘዘ !

በአለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን እስቸኳይ ክስ ተከትሎ በሁለቱ አካላት መካከል ከተደረገው ክርክር በኋላ ዛሬ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡

የአለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እስራኤል በራፋህ ላይ የጀመረችው የመሬት ጥቃት አሁንም እንደቀጠለ እና ለሌላ መፈናቀል ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመጋቢት ወር በፍርድ ቤቱ የፀደቁት ጊዜያዊ እርምጃዎች ለቅርብ ጊዜ ለውጦች ሙሉ ለሙሉ ምላሽ እንደማይሰጡ ተናግረዋል, ስለዚህም ለውጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በዚህም የእስራኤል እና የፍልስጤም ጦርነትን በሚመለከት የተወሰዱትን ቀደምት ጊዜያዊ እርምጃዎችን ለመቀየር እና ተጨማሪ አዳዲስ ህጎችን ለመጨመር በደቡብ አፍሪካ የቀረበው ጥያቄ ትክክል ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተቀረው የጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም ወይም ጦርነት ማቆምን በተመለከተ ምንም አይነት ውሳኔ አላሳለፈም።

የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ሃላፊ ነዋፍ ሰላም እስራኤል በራፋህ የምታደርገውን ጥቃት ለማስቆም ደቡብ አፍሪካ ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ውሳኔ በሰጡበት ቅጽበት።

"እስራኤል በጋዛ የሚገኘውን የፍልስጤም ህዝብ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል በራፋ ግዛት ውስጥ የምታደርገውን ወታደራዊ ጥቃትም ሆነ ሌላ እርምጃዋን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ማቆም አለባት።"

በተጨማሪም ፣ “ ያለ ምንም እንቅፋት ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባትን ለማረጋገጥ ውጤታማ እርምጃዎችን መተግበር እና በማንኛውም የተባበሩት መንግስታት የሚመለከታቸው አካላት የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲመረምር፣ መረጃ ፍለጋ ተልዕኮ ወይም ምርመራ እንዲከናወን መፍቀድ አለባት ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት በ 13 ድጋፍ እና 2 ተቃውሞ እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ወታደራዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንድታቆም አዟል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በቴልግም መከታተል ትችላላችሁ https://t.me/Alif_Online_Official

የሙሐመድ ትውልድ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group