Translation is not possible.

አላህዬ

እኔ አውቃለሁ የዋልክልኝን ውለታ፡

አልሀምዱ ሊላህ የኔ ጌታ፡

ውስጤ ያውቃል ያደረክልኝን ስራ፡

ስንቴ አዳንከኝ ከስንቱ ዘግናኝ መከራ....

በምን አቅሜ እንደት ብዬ ልለምንህ፡

የኔ ጌታ ግን በርግጠኝነት ነው የማምንህ፡

አውቃለሁ ለምኘህ አታሳፍረኝም፡

ስጠራህ ሰማኸኝ አልተፀየፍከኝም፡

በምን አንደበት ደስታየን በምን ልግለፀው፡

እንደት ይነገር ደስታዬ በልቤ የተቀረፀው...!?

«አላህዬ ብቻ ሽኩር ይገባህ»

Send as a message
Share on my page
Share in the group