Translation is not possible.

✍በሚስት ቅናቻ የተነሳ የተቃጠሉ ኪታቦች

📕የቋንቋው ሊቅ ሲበወይህ………

እሱ ኪታቦችን በመፃፍ እና በማጥናት ይወጠርና ሚስቱን ችላ ችላ ይላት ነበር።

በዚህ የተናደደችው ሚስቱ አንድ ቀን ኪታቦቹን ሰብስባ አቃጠለችበት።

እሱም የሰራችውን ሲያይ በድንጋጤ ራሱን ሳተ።

  ከፌንት ሲነቃ "ፈትቼሻለሁ" ብሎ ሸኛት።

📕ኢብራሂም አል_ዓያሽ የተባለው………

ሀያ ዐመታት ድረስ "خجرات النساء" የተሰኘው ኪታቡን ሲፅፍ ከቆየ በኋላ "በኪታቡ ተወጥሮ እኔን ረስቶኛል" ያለችው ሚስት ይህንን ሁሉ ዐመት የደከመበት ኪታብ ሰብስባ አቃጠለችው።

  እሱም በዚሁ ድንጋጤ ሽባ ሆኖ ቀረ።

📕ኣሙሪያህ የተባለችዋ ግዛት ንጉስ የነበረው መሕሙድ………

ኪታቦችን በማንበብ እና በማጥናት ቢዚ ይሆን ነበር። በዚህም የተናደደችው ሚስቱ የሞተ ቀን ኪታቦቹን ሰብስባ "አብራችሁ ተቀበሩ" በሚመስል መልኩ ወደ ኩሬ ውሀ ስትወረውር ተስተውላለች።

📕ለይስ ቢን ሙዘፈር………

የተባለው ፀሀፊም ኪታቦቻቸው በሚስቶቻቸው ቅናት ከተቃጠሉባቸው ተርታ ይወሳል።

📕የምታውቁት ትልቁ ኢማም ኢማሙ ዙህሪይ………

ሚስቱ "ወላሂ እነዚህ ኪታቦችህ ከሦስት ጣኡንት በላይ እኔ ላይ የከፉ ናቸው" እንዳለችው ተጠቅሷል።

ይህንን ያነበቡ የዘመናችን ሴቶችም………

   "እነዝያ ሴቶች አላህ ይዘንላቸውና ይህንን እርምጃ ባይወስዱ ኖሮ: ዛሬም ባሎቻችን እነዝያ ኪታቦች እያነበቡ እኛን ይረሱን ነበር" ማለታቸው ተዘግቧል።

በዘመናችን ደግሞ………

   በሚስት ቅናቻ ተወርውረው የሚሰበሩ ስልኮች ቤት ይቁጠራቸው።

🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍🔍

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group