ደጋግመው ሲነግሩንና ስንሰማው ከረምንና ሁሉም ነገር ተራ ሆነብን። ከልጅነታችን ጀምሮ የቁርኣንን አንዲት ሐርፍ ያነበበ 10 ምንዳ ይጻፍለታል እየተባለ ሲነገረን አደግንና በቃ ተራ ቀልድ መስሎን ቀረ። ጊዜያችንን በፌስቡክ፣ በቴሌ ግራምና መሰል ነገሮች መጨረስ ሆነ ስራችን። በቀን አምስቴ ውዱእ ማድረግ ከወንጀል በዚያው ልክ መፅዳት እንዳለ ሲነገረን አደግንና ይሀው ዛሬ ትዝም ሊለን አልቻለም። ሀሳባችን ሁሉ ስለተቃራኒ ፆታ፣ ስለ ተከታታይ ፊልም፣ ስለገንዘብ፣ ስለፖለቲካ፣ ስለዘር፣ ስለምቾታችንና አለባበሳችን ሆኗል።
ሌሊት ተነስቶ መስገድ ቀረ! የሱና ፆሞች ላይ ተዳከምን! ለዒልም ከመሯሯጥ ሰለቸን! ሱሪ ማሳጠርና ፂም ማሳደግ ቀርቶ ሶላህ እንኳ በአግባቡ መስገድ አልቻልንም። ጀልባብ መልበስ በሆነ ወቅት የቀረ ፋሽን ተደረገና ለተወሰነ ጊዜ ከላይ ሻርብ ይጠመጠማል። ከዚያም በሂደት የሚያጣብቁ አልባሳት ይጀመራሉ። በቃ ሐዲሥ ሲነገረን የሆነ ዝም ብሎ የሚለፈልፍ ሰው ከፊታችን ያለ እየመሰለን ነው። በየቀኑ ኪታቦች እየተባዙ ነው። የሚያነባቸው ከየት ይምጣ?! ወንዱ የሴት ፎቶ ያገላብጣል። ሴቷ የወንድ ፎቶ! ሲነጋ እኔ እበልጣለሁ በዱንያ፣ እኔ እበልጣለሁ በውበት፣ እኔ እበልጣለሁ በአለባበስ፣ እኔ እበልጣለሁ በዝና ሆነ ሩጫው። ሲመሽ የፈረደበት ቴሌቭዥን ለይ እንጣዳለን! ሲነጋ በድብርትና በመጥፎ ዓላማ ከቤት እንወጣለን።
በቃ አላህ እድሜ በሰጠን ቁጥር ወደርሱ መቅረብ ሳይሆን ጭራሽ ሞትን ፈርተን ከሞት የምናመልጥ እመሰለን በጊዜያዊ ስሜቶች ውስጥ ተደብቀን ለመቆየት እየጣርን ነው። ማናችን ነን እስኪ ቀብር አስፈርቶን እያቀስን ያለነው!? ማነው እስኪ የአላህ ፍቅር ማርኮት እያነባ ያለው?! ማናችን ነን እስኪ የጀነት ጉጉት አድሮብን አላህን የምንገዛው?! ማነው እስኪ አጅ ነቢ ቀና ብሎ ላለማየት እየተጣጣረ ያለው?! እስኪ በንግዳችን ሳንዋሽ እየሰራን ነው ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። ትምህርት ቤት የምንሄደውስ ለምንድ ነው? የወላጆችን ሐቅስ እንዴት እያደረግን ነው? አንደ እንስሳ እንዲሁ መኖር ይሰለቻል ወላሂ!
۞ أَلَمْ يَأْنِ لِلَّذِينَ آمَنُوا أَن تَخْشَعَ قُلُوبُهُمْ لِذِكْرِ اللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ الْحَقِّ وَلَا يَكُونُوا كَالَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلُ فَطَالَ عَلَيْهِمُ الْأَمَدُ فَقَسَتْ قُلُوبُهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ
(ሱረቱ አል-ሐዲድ - 16)
ለነዚያ ለአመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው ልቦቻቸው ሊፈሩ እንደእነዚያም በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ እንደረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁት ላይኾኑ (ጊዜው) አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡
https://t.me/keselefochkote