Translation is not possible.

🧿ባሎች ሁለት ዐይነት ናቸው ይላሉ………

1ኛው, ሸጋ ባል ነው፦

ሚስቱ ሁሌም ገና ጨቅላ እንደሆነች እንዲሰማት የሚያጫውታት, እንደ ህፃን የሚያቃልዳት ይሆንና ተንከባክቦ እንደ ፅጌሬዳ እንቡጥ ያስውባታል።

2ኛው, ክፉ ባል ነው፦

ሚስቱን በንዝንዝ እና በጭቅጭቅ ያስረጃትና ከእሱ በአስርት ዐመታት የምትበልጥ አሮጊት አስመስሎ ያስረጃታል።

ሴት ልጅ………

ውስን በሆነ ዐመት ታረጃለች ወይም ውስን በሆነ ዐመት ታብባለች ማለት ስህተት ነው።

እውነታው………

ሴት ልጅ ከጥሩ ባል ጋ ከሆነች ሁሌም ታብባለች:

ከክፉ ባል ጋ ከሆነች በልጅነቷም ትጠወልጋለች።

መታወቅ ያለበት………

ትዳር የሚገነባው በሴቷ ውበት ወይም በወንዱ ሀብት አይደለም። ከጊዜ በኋላ የእሷ ውበትም ይረግፋል, የእሱ አቅምም ይደክማል። አብሮነታቸው አስተሳስሮ ሊያስቀጥል የሚችል ነገር ቢኖር: በመሃላቸው ያለው

መዋደድ እና መተዛዘን ነው!!

ይህ ከሆነ………

ሴቷ የወንዱ አደራ: ወንዱም የሴቷ መከታ ሆነው ይኖራሉ!!

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group