♻️ 🔻🇵🇸 🟢 አልቃሳም ብርጌድ በመግለጫው "በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ በጀባሊያ ካምፕ ትምህርት ቤቶች ጎዳና መጨረሻ ላይ በሚገኝ ቤት ውስጥ የመሸገውን ልዩ የጽዮናውያን ኃይል እጅግ ውስብስብ በሆነ ኦፕሬሺንሺን በፀረ-ሰው ሚሳኤል ኢላማ አድርጓል። በሰአቱ የጠላት ወታደሮች የታችኛውን የቤቱን ክፍል ለቀው ሲወጡ “በራአዲያ”  ፈንጂ ኢላማ ተደርገው ተገድለዋል እንዲሁም ቆስለዋል።

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ብዙ ወታደሮች ጥቃቱን ወደፈፀሙት ሙጃሂዲኖቻችን ተጠጉ ተዋጊዎቹም ወደ ቤቱ በማቅናት በቤቱ መግቢያ ላይ ፀረ-ሰው ፈንጅ በማፈንዳት ተጨማሪ ሞት እና የአካል ጉዳት ማድረሳቸውን ወዲያውኑም የጽዮናውያኑ ጦር የተጎዱትን ለመታደግ እና የሞቱትን ለማንሳት ወደ አከባቢው ሲደርሱ መርካቫ ታንካቸውን “በአል-ያሲን 105” ላውንቸር ኢላማ አድርገው ሲመቱ ሁለተኛውን ታንክ ደግሞ በ’ሹአት’ ፈንጂ አፈንድተዋል ሲል አል ቀሳም አስታውቋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን በቴልግም መከታተል ትችላላችሁ https://t.me/Alif_Online_Official

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group