#ወንጀል የማይሰራ አያንብበው
#አንድ ሰው ኢብራሂም ኢብን አድሐም ጋር ይመጣና “ራሴን መቆጣጠር አልቻልኩም፤ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ወንጀል ውስጥ እወድቃለሁ፤ ምከሩኝ“ አላቸው፡፡ ኢብራሂም “እነዚህን አምስት ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላህና ስራ ላይ ካዋልካቸው እርግጠኛ ነኝ ተመልሰህ ወንጀሉ ላይ አትወድቅም” አሉት፡፡ ልጁም “ንገሩኝ እተገብረዋለሁ” ይላቸዋል ኢብራሂም “እንግዲህ የመጀመሪያው… አላህ ላይ ማመጵን የፈለግክ ጊዜ ከሱ ምግብ እንዳትበላ” ልጁ “እንዴ አለም ላይ ያሉ ሁሉ በሱ ነው ሚረዘቁት ታዲያ ከየት አምጥቼ እበላለሁ ?”
#ኢብራሂም “ታዲያ ከራሱ በመጣ ርዝቅ እየተመገብክ በሱ ላይ ማመጱ አግባብ ነውን ?” ልጁ “በፍጱም አግባብ አይደለም፤ ባይሆን ሁለተኛውን ንገሩኝ” ኢብራሂም “አላህን ማመጵ የሻህ ጊዜ ከሱ መሬት ራቅ ብለህ ፈጵመው” ልጁ “ኢብራሂም ይህማ በፍጱም አይቻልም!! ሁሉ መሬት የሱ አይደል እንዴ የት ሄጄ ልኖር ?” ኢብራሂም “ታዲያ በሱ መሬት እየኖርክ የሱን ምግብ እየበላህ በሱ ማመጱስ አግባብ ነው?” ልጁ “በፍጱም አይደለም!! ሶስተኛውን ንገሩኝ”
#ኢብራሂም “የሱን ምግብ እየበላህም ይሁን በራሱ መሬት እየኖርክ ወንጀል መስራት ስትፈልግ እሱ የማያይህ ቦታ #ደበቅ ብለህ ፈጵመው” ልጁ “ምን ማለትህ ነው ኢብራሂም ? እንኳን እኔን አይደል ጨለማ ላይ ያለችን ጥቁር ጉንዳን ብትሆን ከሱ እይታ መች ታመልጥና” ኢብራሂም “ታዲያ የሱን ምግብ እየበላህ፣ በሱ መሬት እየኖርክ፣ እንደሚያይህ እያወቅክ በሱ ማመጱ አግባብ ነው?” ልጁ “በፍጱም አግባብ አይደለም!! አራተኛውን ይንገሩኝ” #ኢብራሂም “የሞት መላዕክት ወዳንተ ሲመጣ “ትንሽ ጊዜ ስጠኝና ተውበት አድርጌ አላህን እንደሚፈልገው ልገዛ” በለው” ልጁ “እንዴ ኢብራሂም አይሰማኝማ”
#ኢብራሂም “የምትሞተው መች እንደሆነ ሳታውቅ፤ #ሞት ከመጣ በሗላ ተውበት ብታደርግ እንደማይሰማህ እያወቅክ በሱ ላይ ማመጱ አግባብ ነው ?” ልጁ “አይደለም አይደለም በፍጱም አይደለም!!! አምስተኛው ምንድነው?” ኢብራሂም “የእሳት መላዕክቶች እሳት ሊከቱህ ሲመጡ ከነሱ ጋር እንዳትሄድ” ልጁ “በቃህ በቃህ ኢብራሂም!!! ወደድኩም ጠላሁም አንጠልጥለው ይወስዱኝ የለ?” ኢብራሂም “ታዲያ ይህን ሁሉ እያወቅክ በአላህ ላይ ማመጱ አግባብ ነው ?”
#ልጁ ጎንበስ ብሎ እያለቀሰ “#ጌታዬ ምህረትህን ጌታዬ ይቅርታህን” በማለት ከልቡ ወደ አላህ ተመለሰ... #gaza #freepalestine #quran #palestine