Translation is not possible.

"አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የቂያማ ቀን እንዲህ ይላል፦

(ለክብሬ የተዋደዱ የታሉ?!) ዛሬ የማንም ጥላ በሌለበት ቀን በጥላዬ ሥር አስጠልላቸዋለሁ።"

ነብያችን(ﷺ)

(ሙስሊም:2566)

#ጓደኝነት አላህን ፈሪ ጓደኛ ያለው ሰው ትረፉ የበዛ ነው::መልካም ጓደኛ ከትላልቅ የአላህ ፀጋወች መካከል አንዱ ነው::ጓደኝነት መተሳሰብ ነው።

አንዱ የሚጠቀምበት ሌላኛው የሚጎዳበት፣ አንዱ የሚሰጥበት ሌላው የሚቀበልበት፣ አንዱ ንጉሥ የሚሆንበት ሌላው የሚገብርበት መድረክ አይደለም።

ጓደኝነታችሁ ሌላዉን የማሞኝነት እና የብልጣብልጥነት አይሁን።ኒያዉም የተበላሸ አይሁን።

ጓደኝነት ዓላማው ትልቅ ነው። ለአላህ ብቻ ብለው የተቀራረቡ ጓደኛሞች የልብ ወንድማማቾች ናቸው። ዛሬን የዱንያን ፈተና ተጋግዘው ይሻገራሉ። ነገም በጀነት አብረው ይገባሉ።

🥀🥀ትክክለኛ ጓደኛ ማለት ፦እሱ ጋር መሆን ስታበዛ ማትሰለቸዉ፤ ስትለየዉ የማይረሳህ፤ ስትቀርበዉ የሚቀርብህ፤ ስትርቀዉ ከአንተ ላለመለየት የሚጥር፤ ዉዴታዉን ከቃላት ሽንገላ ይልቅ በተግባር የሚገልፅልህ ነዉ::

ረሱል (ﷺ)ሲናገሩ "የመልካም ጓደኛ ምሳሌ ከሽቶ ነጋዴ ጋር ስትገናኝ ካለህ ገዝተህ፣ከሌለህ ከሽቶዉ መልካም ጠረን እንደምታገኝ ያህል ነው:: " ብለዋል

🌹💜اَللّٰهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبّيِّنَا مُحَمَّدْﷺ💜🌹

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group