Translation is not possible.

#ሁሉንም_እንስሳት፣ #ጉንዳንን_ጨምሮ #በእሳት_ማቃጠል_ስለመከልከሉ

#ክፍል_2

#ሐዲሥ 283 / 1610

ኢብኑ መስዑድ እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፤ በአንድ ጉዞ ላይ ከአላህ መልዕክተኛ ጋር ነበርን። ለጉዳያቸው ገለል አሉ። ሁለት ልጆች ያሏት አንዲት ወፍ አየን። ሁለቱን ልጆቿን ወሰድንባት። መጣችና ከበላያችን ታንዣባብ ጀመር። ነቢዩ መጡና፦ የዚህችን ወፍ ልጆች የወሰደ ማን ነው?" አሉ። እኛ ያቃጠልነውን የጉንዳን ማዕከልም ተመለከቱ። ማን አቃጠለው?" አሉ። "እኛ ነን" አልናቸው። "በእሳት የማቃጠል መብት ያለው የእሳት አምላክ ብቻ ነው" አሉን። (አቡ ዳውድ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ እንስሳትን ያለሸሪዓዊ አግባብ ማንገላታት ክልክል ስለመሆኑ፤

2/ እንስሳትን፣ ቅማልን ወይም ጉንዳንን እንኳ ሳይቀር በእሳት ማቃጠል ክልክል ነው።

3/ ኢስላም ከሰብአዊ መብት አልፎ ለእንስሳት መብት እንኳ ምን ያህል ተቆርቋሪነት እንደሚያሳይ ይህ እና መሰል የሐዲሥ ዘገባዎች ያመለክታሉ። በእርግጥም ለዓለማት በረከት፡ በእርግጥም ለዓለም እዝነት።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group