Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

የአፕል አመታዊ የተማሪዎች የስዊፍት ውድድር (Apple's Swift Student Challenge) አሸናፊዋ ኒቃቢስት ።

ኒቃቢስቶች ይችላሉ‼😊

================

✍ ኒቃቢስት ሆኖ ፕሮግራመር/ ኮደር/ ደቨሎፐር… መሆን ይቻላል። እንዳውም ሐላል የሆነው ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለሙስሊም ሴቶች ሸሪዓውን የጠበቀ ገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ።

ምክንያቱም ሴት ልጅ በቤቷ እንድትረጋ ሸሪዓው አዟታል። ኢኽቲላጥ ባለበት የሥራ ቦታ ላይ ኑሮን ለማሸነፍ በሚል ከምትጋፈጥ፤ በቤቷ ውስጥ ረግታ ከየትኛውም ሰው በላይ ተከፋይ መሆን ትችላለች።

ስትፈልግ remotely freelancer ሆና መሥራት ትችላለች፣ ሲያሻት ከከስተመር ኦርደሮችን እየተቀበለች በሃገር ውስጥም ከቤቷ ሆና መሥራት ትችላለች።

ከተቃራኒ ጾታ ጋር ንክኪ ሳይኖረው የተሻለ ሐላል ገቢ ማግኘት ትችላለች። በዚህ መልክ ለመሥራት ደግሞ እንደዚህ የቴክኖሎጂ መስክ የተሻለ የለም።

የሃገረ ሳዑዲ ዓረቢያ ዜጋ የሆነችው ኒቃቢስቲቷ እህት ጀዋሂር "My Child" የተሰኘ አፕ ሠርታ አበርክታለች። አፑ የሚንተባተቡ (stuttering) ልጆችን የመናገር ክህሎት ለማዳበር የሚያግዝ ነው።

እህታችን የአሜሪካው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው የአፕል አመታዊ የተማሪዎች የስዊፍት ውድድር (Apple's Swift Student Challenge) አሸናፊ ሆናለች።

Jawaher Shaman from Saudi Arabia 🇸🇦 created her app My Child to help children with speech conditions.

Love Niqabi Coders❤️!

ዝርዝሩን ከአፕል ድረ ገፅ ዜና ላይ አንብቡ።

Link: https://www.apple.com/newsroom..../2024/05/meet-three-

Via. Murad Tadese

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас