Translation is not possible.

ዳታ ማይኒንግ ምን ዓይነት ጠቀሜታ አለው?

ዳታ ማይኒንግ ከግዙፍ ዳታ ውስጥ ጠቃሚውን ብቻ ለይቶ ለማውጣት ከመረጃ ክምር መካከል እንደመቆፈር የሚቆጠር ነው፡፡ ይህም ብዙ መጠን ያለውን ዳታ በመመርመር እና በመተንተን በተለያዩ መስኮች ችግር ፈቺና ትርጉም አዘል መረጃዎችን ለይቶ ለማወቅ አበርክቶው ከፍ ያለ ዘርፍ እንዲሆን አስችሎታል፡፡

ከመረጃዎች መካከል ምስጢሮችን እንደሚያነፈንፍ የፖሊስ መርማሪ በዳታ ማይኒንግ ሂደትም የተደበቁ ቁልፍ መረጃዎችን ለመለየት ስታቲስቲክስ፣ ማሽን ለርኒንግ፣ ዲፕ ለርኒንግ እና የተለያዩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ስልቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

በዘርፉ አሜሪካ፣ ቻይና፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እና እስራዔል ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ እና ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት ከሚሰሩ ሀገራት መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

ተመራማሪዎች፣ የንግድ ተቋማት እንዲሁም መንግሥታት በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔን እንዲያሳልፉ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው የሳይንስ ዳይሬክት ድረ-ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዳታ ማይኒንግ እንደ ጤናና ትምህርት ባሉት መስኮች የሚያጠነጥኑ መረጃዎችን በተገቢ መልኩ በመረዳት ዜጋ ተኮር ስራዎች ላይ ለመስራት ዕድል ይፈጥራል፡፡ አገልግሎት ሰጪ እና በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማትም የደንበኞችን ፍላጎት በማወቅ እርካታን ለማሳደግ እንዲችሉ ጉልህ ሚና አለው፡፡

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group