Translation is not possible.

"ሁሉም ሰው በፖለቲካ ተጠምዷል። ፖለቲከኞች ሲቀሩ። እነሱ ግን በንግድ ነው የተጠመዱት።"

* ዐብዱል መሊክ አልኢብቢ *

·

·

መሪር ሐቅ!! አብዛኞቻችን የፖለቲካው ማእበል ወስዶን ከዚያ ከዚህ እያላጋን ነው። አንዳንዱማ ከሃይማኖቱ በላይ ዘሩን እያስቀደመ የቆሻሻ ፖለቲካ ጎርፍ ወስዶታል።

ፖለቲከኞቹስ? አብዛኞቹ የሞቀ ንግድ ላይ ናቸው። እንጀራቸውን ሊያበስሉ ተፍ ተፍ እያሉ ነው። ከመንግሥት በተቃዋሚ ስም፣ ከህዝብ በነፃነት ትግል ስም፣ ከውጭ በሰብአዊ መብት ቅስቀሳ ስም ከያቅጣጫው ይዘርፋሉ። ለምስኪን ተፈናቃዮች የተሰበሰበን እርዳታ ይነጥቃሉ።

በነሱ የፖለቲካ ጦስ የሚሞተው፣ የሚፈናቀለው፣ የሚጎዳው ግን ፖለቲከኞቹ ሳይሆኑ ህዝቡ ነው። ለዘመናት ተዋልዶ፣ ተጋምዶ የኖረ ህዝብ የፖለቲከኞች ድግምት ከተደገመበት በኋላ ፍፁም በማይታሰብ መልኩ አንዱ ሌላውን ያርዳል፤ ይሰቅላል፤ ያቃጥላል፤ ይወግራል፤ በጅምላ ያፈናቅላል። ፖለቲከኞቹ ግን በህዝብ እልቂት ገበያቸው ይደራል። በህዝብ መፈናቀል ንግዳቸው ይደምቃል። በኛ ስም በጮሁ ቁጥር ለኛ የተቆረቆሩ እየመሰለን ጆሯችንን እንሰጣቸዋለን። "ማንም በክፉ አይንካቸው" እንላለን። ፎቷቸውን አሳትመን እንለብሳለን፤ እንለጥፋለን፤ እንሰቅላለን። ግና ህዝብ እየከሳ እነሱ ይደልባሉ። ህዝብ እየተፈናቀለ እነሱ ለአይን ከሚያሳሳ ሰገነት መግለጫ ይሰጣሉ። የህዝብ ልጅ ወደ ትግል፣ የነሱ ልጆች ወደ ውድ ትምህርት ተቋማት። ህዝብ ወደ ታች እነሱ ወደ ላይ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 9/2011)

=

የቴሌግራም ቻናል :-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group