Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

♻️ 🇵🇸 ⚡🏴‍☠️ የሐማስ ከባድ ጥቃት!

ሐማስ በቀጥታ በ"ከረም ሻሎም" ወይም ከረም አቡ ሳሊም የሚገኘውን የእስራኤል ወታደራዊ ካምፕ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሲፈፅም ቢያንስ10 ሮኬቶችን ተጠቅሞ ሲሆን ቢያንስ 10 የእስራኤል ወታደሮች ቆስለዋል 3 ሞተዋል እንዲሁም 4 ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

አንድ የጽዮናውያን ምንጭ እንዲህ ሲል ጽፏል "ሐማስ የእስረኛ ልውውጥ ሀሳቡ ላለመሳካቱ የሰጠው ምላሽ 'በከረም ሻሎም' ላይ የወታደሮችን አስክሬን ለኔታንያሁ መስጠት ሆኗል" ብሏል።

ለአል-አቅሳ ቲቪ የጸጥታ እና የግንባር ምንጮች እንዳሳወቁት ከተቃውሞው በተገኘው መረጃ ቢያንስ 3 ወታደሮች መሞታቸውን እና ሌሎች 10 ወታደሮች ከመካከለኛ እስከ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘግቧል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በራፋ ለሚጀመረው ወረራ መቆጣጠሪያ እንዲሆን እና የሺን ቤት መኮንኖችን ጨምሮ የእስራኤል ጀነራሎች እንዲቆዩበትና የራፋህ ኦፕሬሽንን ለማቀድ ታስቦ በተዘጋጀው "ከከረም ሻሎም" ወታደራዊ ጣቢያ በስተምስራቅ የሚገኘው የጽዮናውያን ኮማንድ ፖስት ላይ ነው::

ተከታታይ ጥቃት ይፈፀማል በሚል ስጋት ቢያንስ ለአንድ ሰአት ያህል የሞቱትን እና የቆሰሉትን ለማግኝት ምንም ሙከራ ሳይደረግ ቆይቷል።

ቴሌግራም https://t.me/+JCPgkAudChZhMzZk

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group