አለፍኩ ስል ደረስኩ ስቀር ወደኋላ
ፀናሁ ስል ጠነከርኩ ሲያሸንፈኝ ጘፍላ
ቆምኩኝ ስል ስወድቅ ጠብቋል ስል ሲላላ
የራሴ ፈራርሶ ስጠግን ለሌላ
አለሁ በጎደሎ ዛሬየም ሳይሞላ።
አስታራቂ ጠፍቶ ልቤን አስጨንቆት
ሰላሜ ተነስቶ ደስታየንም ሰርቆት
እፎይታ ስጠብቅ ልቤ ፈላሕ ናፍቆት
ድሎት እየታየኝ ቀምቶ ደብቆት
የኔው ለኔው በደል ስኬቴን አርቆት
ታይ ታረቂኝ ነፍሴ ከኔጋ እንስማማ
ትዛዜን ተቀበይ እሽ በይኝ’ማ
ቢሆን እንማከር እንወያይማ
እጅ ስጭ ላንችው ነው አትሁኚ ጠማማ
ተደግሶልሻል የቀብር ጨለማ
መብራት አታገኚ ኩራዝ የለ ሻማ
ሰው የለ ገላጋይ ጩኸት የሚሰማ
ዛሬ ተስተካከይ ለመሆን ትርፋማ
ምርጫውና እድልሽ ዛሬ ሁኖ ቀኑ
ለምንስ ያታልሽ ያዱ፞ኒያ ፋሽኑ
ለዚህ ላጭር እድሜ ብዙ መሽሞንሞኑ
አርቆ ማሰቡ ህልም መደቀኑ
ልብ ግዥ ነፍሴ ተመለሽ አሁኑ።
አንድ በይ ከስብሽን ካሁኑ ጀምሪ
በጀነት ፀጋዎች እንድትበሰሪ
ቅድሚያ ስጭ ለዲንሽ በታዘዝሽው ስሪ፣
ከመጥፎ ተገለሽ ለመልካም ተገሪ፣
ለነገዋ ቤትሽ ስንቅሽን አኑሪ።
🖊 #ቢንት_ሙሐመድ
አለፍኩ ስል ደረስኩ ስቀር ወደኋላ
ፀናሁ ስል ጠነከርኩ ሲያሸንፈኝ ጘፍላ
ቆምኩኝ ስል ስወድቅ ጠብቋል ስል ሲላላ
የራሴ ፈራርሶ ስጠግን ለሌላ
አለሁ በጎደሎ ዛሬየም ሳይሞላ።
አስታራቂ ጠፍቶ ልቤን አስጨንቆት
ሰላሜ ተነስቶ ደስታየንም ሰርቆት
እፎይታ ስጠብቅ ልቤ ፈላሕ ናፍቆት
ድሎት እየታየኝ ቀምቶ ደብቆት
የኔው ለኔው በደል ስኬቴን አርቆት
ታይ ታረቂኝ ነፍሴ ከኔጋ እንስማማ
ትዛዜን ተቀበይ እሽ በይኝ’ማ
ቢሆን እንማከር እንወያይማ
እጅ ስጭ ላንችው ነው አትሁኚ ጠማማ
ተደግሶልሻል የቀብር ጨለማ
መብራት አታገኚ ኩራዝ የለ ሻማ
ሰው የለ ገላጋይ ጩኸት የሚሰማ
ዛሬ ተስተካከይ ለመሆን ትርፋማ
ምርጫውና እድልሽ ዛሬ ሁኖ ቀኑ
ለምንስ ያታልሽ ያዱ፞ኒያ ፋሽኑ
ለዚህ ላጭር እድሜ ብዙ መሽሞንሞኑ
አርቆ ማሰቡ ህልም መደቀኑ
ልብ ግዥ ነፍሴ ተመለሽ አሁኑ።
አንድ በይ ከስብሽን ካሁኑ ጀምሪ
በጀነት ፀጋዎች እንድትበሰሪ
ቅድሚያ ስጭ ለዲንሽ በታዘዝሽው ስሪ፣
ከመጥፎ ተገለሽ ለመልካም ተገሪ፣
ለነገዋ ቤትሽ ስንቅሽን አኑሪ።
🖊 #ቢንት_ሙሐመድ