Translation is not possible.

ምን ነው ይህን ፓርክ ሰሜንን እንደ እንጀራ ልጅ ታዩታላችሁ⁉️

*****

ፓርኩ ስንቴ ነደደ? የሰሜን ተራራዎች ሁሌ በሚባል መልኩ ከየካቲት እስከ ሚያዚያ ባሉ ወራቶች ቃጠሎ ይፈፀምበታል። 2011 ፓርኩ #ግጭ አካባቢ ተቃጥሎ፡ እሳቱ ከቁጥጥር ዉጭ ሁኖ ከኬንያ 1200 ሊትር ዉሃ የመሸከም አቅም ያላትን ጀት በመዋስ፡ (በክፍያ አለመሆኑን እርግጠኛ አይደለሁም)፣ ይህች ጀት ከአሰራ ውሃ ብታመላልስም ጠብ እሚል ነገር አልመጣም፡ ደርሳ እስክትመለስ እሳቱ አገርሽቷል። የሰለጠነ እሳት ተከላካይ ስሌለለን 9 ኢስራኤላዊ በጎ ፍቃደኞችን አግኝተን፡ ጥረቱ እምብዛም ዉጤት ሳያመጣ #ዝናብ በመዝነቡ ምክኒያት እሳቱ ሊጠፋ ችሏል። , 2012 እንዲሁ #ጠቀራው_ዱር ተቃጥሎ በህዝቡ ርብርብ ሊጠፋ ችሏል። እነዚህ ቃጠሎዎች ለአብነት ያክል እንጅ ፓርኩማ ሁሌ እሳት ነው በቃ። ለፓርኩ ሲሉ የህይወት መስዋእትነት እሚከፍሉትም ብዙ ናቸው። ,

አንድ ጊዜ እንኳ ፓርኩ ፍትህ መች አገኘና፡ ማነው ይህን ፓርክ እሚያቃጥለው⁉️ ዝም ብለህ ማህበረሰቡ ይመስል ማህበረሰቡ እንዳትል፡ የት አለ ማስረጃህ? ፓርኩ ይህን ያክል ጊዜ ሲለኮስ የት አለ አንዴ እንኳ ያገኘው ፍትህ?

ያሉት የመንግስት ተቋማቶች ከፓርኩ ጥቅም ብቻ ሳይሆን ምን ስራ ሰሩ? የት አለ የሰሩት መሰረተ ልማት?

#ምን_ነው_ይህን_ፓርክ_ሰሜንን_እንደ_እንጀራ_ልጅ_ታዩታላችሁ፡ ይህ እኮ #ፖሌቲካ አይደለም፡ የሀገር ብሎም #የአለም_ቅርስ ነው።አንዱ #በቁጥጥር ስር ውሏል፡ አንደኛው በቁጥጥር ስር ለማድረግ #እርብርብ_ላይ ነን። ሀይ አቃጣዩን ወይንስ እሳቱን። ሌላኛው ደግሞ #መልሶ_አገርሽቷል። እረ ለመሆኑ ስታወራላቸው የነበሩት #የደህንነት_ካሜራዎች የት ሄዱ?

📝እናም እምትሰማኝ ከሆንክ እነዚህን ምክረ ሀሳብ እረ እንጃልህ እንጅ እንካልህ።

✔️ለፓርኩ #መሰረተ_ልማት መስራት፡ ከአይና ሜዳ እስከ እናትየ ፡ ከሳንቃብር እስከ ቀበርቾው መጫርያ፡ ከድንግል ሜዳ በጅንባር ወንዝ ወደ ቀዳዲት፣ ሙጭላ አፋፍና እሜት ጎጎ ለአጋ ጊዜ ብቻ እሚሆን መንገድ መስራት አደጋ ቢከሰ ሰዎችን በፍጥነት ለማጓጓዝ ይጠቅማል፤

✔️ከጅንባር #ውሃ በመውሰድ አደገኛ በሚባሉ ቦታዎች ጫካዎች፣ ማማዎችና ገደሉች የውሃ መስመር መዘርጋት፤

✔️ለፓርኩ ቋሚ #የሰለጠነ እሳት ተከላካይ መመደብ፤

✔️የትም አይነት ውሳኔዎች ሲኖሩ ማህበረሰቡን ማካተት፤

✔️የደህንነት ካሜራውች በትክክለኛው ቦታና ብዛት ማስቀመጥ፤

✔️ፓርኩ ውስጥ ሙስናን ማስወገድ። ሌላም ሌላም።ሚዲያ፡

እና አሁንም #እልሀለሁ #ሚዲያ፡ #ባለስልጣን #አስጎብኝ #አክቲቪስት #በቃ_ሁልህም #የሰሜን_ተራራዎች_ብሄራዊ_ፓርክን_እንደ_እንጀራ_ልጅ_አትየው።

image
image
image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group