لا يمكن الترجمة

✍️ ሁለት የቢድዐ ከባድ አደጋዎች

⚫️አንደኛው;

🔥የአላህ ንግግር ማስዋሸት ነው‼️

አላህ በተከበረው ቃሉ

{الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ}

{በዛሬው ዕለት ዲናችሁን ሞላሁላችሁ}

ብሎ ይህ እስልምና ምንም ዐይነት ጉድለት የሌለበት ሀይማኖት እንደሆነ ይነግረናል።

ዛሬ አንድ ሰው ተነስቶ………

“ይህ ነገር እስልምና ውስጥ ቢጨመር ጠቀሜታ ይኖረዋል።”

ብሎ አዲስ ነገር ከፈጠረ ይህ ሰው በምላሱ ባይናገረውም በተግባሩ;

“አላህ ሙሉ ነው ያለን ዲን ሙሉ ሳይሆን ነው።”

የሚል መልእክት ይሰጠናል።

⚫️ሁለተኛው;

🔥የአላህ መልእክተኛ ﷺን መተቸት ነው‼️

አንድ ሰው እስልምና ውስጥ የአላህ መልእክተኛﷺ ያልሰሩት የሆነ ነገር………

“ይህ ነገር ለእስልምና ይጠቅማል።”

ብሎ ቢሰራ በንግግሩ ባይናገረውም በተግባሩ;

“የአላህ መልእክተኛﷺ ዲኑን ጨርሰው አላስተላለፉም።” የሚል ክፉ ግንዛቤ ይሰጣል።

እነዚህ ሁለት ነጥቦች አንድ ሰው አንድ ቢድዐ በመስራቱ የሚወድቅባቸው የከፉ አደጋዎች ናቸው። ቢድዐ ላይ የወደቀ ሰው እነዚህ ነጥቦች ተብራርተውለት "አዎን!" ብሎ ካረጋገጠ ቁርኣን በማስተባበሉና ነብዩﷺን በጉድለት በመተቸቱ ከእስልምና ይወጣል።

ስለሆነም;

የሸዋል ዒድም በለው ቲንሹ ዒድ ከሚለው ጀምሮ አጠቃላይ የቢድዐ ባንዲራ ተሸካሚ ይህንን ቆም ብሎ ሊያይ ይገባዋል!!

👇 👇 👇 👇

ወደ ኸይር ያመላከተ የሰሪው ምንዳ ያገኛል

👆 👆 👆 👆

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة