Translation is not possible.

#አላህን_ለማስታወስ_አዘውትሮ #መሰባሰብ_ተወዳጅ_ተግባር #ስለ_መሆኑና #ካለ_ምክንያት #አላህን_ከማስታወስ_ስብስቦች #መልለየት_ስለመከልከሉ

#ክፍል_2

#ሐዲሥ 247 / 1448

አቡ ሁረይራ እና አቡ ሰዒድ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ "ሰዎች አላህን ለማስታወስ ሲቀመጡ መላኢኮች ይከቧቸዋል። መረጋጋት ይወርድላቸዋል። አላህ ከርሱ ዘንድ ካሉት ፍጡራን ዘንድ ያወሳቸዋል።" (ሙስሊም)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ለዚክር መሰባሰብና መቀማመጥ የላቀ ደረጃ አለው። የአላህን እዝነትና በረከት ለማግኘት፣ ስክነትንና መረጋጋትን ለመጎናጸፍ ይረዳል።

2/ መላእክት የዚክር ስብስቦችን መክበባቸው ለስብስቦቹ ያላቸውን ክብር ለመግለጽ ነው።

3/ አላህን በጋራ ተሰባስበውም ሆነ በግል የሚያወሱ ሰዎች ልቅናቸው ተመልክቷል።

Umma Life

https://ummalife.com/MuslimEthio

ቴሌግራም/ telegram/

https://t.me/ethiomuslim_1

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group