Translation is not possible.

🌹ሚስት ለባሏ ማድረግ የሚጠበቅባት 15 ነገሮች 🌹

ኢማሙ ዘሀቢይ እንዲህ አሉ፦

አንዲት ሚስት ለባሏ መድረግ ከሚጠበቅባት ነገሮች መካከል ፡

1. ሁሌም ከርሱ ሀያዕ ሊኖራት ይገባል

2. እርሱ ፊት ስትሆን አይኗን መስበር አለባት

3. የርሱን ትዕዛዝ እሺ ብላ መታዘዝ አለባት

4. እርሱ በሚናገር ሰአት ፀጥ ማለት አለባት

5. እርሱ ከውጭ ወደቤት በሚገባ ጊዜ ቁማ መቀበል አለባት

6. እርሱን ከሚያስቆጡ ነገሮች ሁሉ መራቅ አለባት

7. እርሱ ከቤት በሚወጣ ጊዜ ሲቆም አብራው ቁማ ልትሸኘው ይገባል

8. እርሱ ልክ ማታ ላይ ሊተኛ ሲል ነፍሷን ልታቀርብለት ይገባል (ማለትም ያን ነገር ማድረግ ሚፈልግ ከሆነ ይሄው አለሁልህ ... ሃሃ)

9. እርሱ ከቤት ወይንም ከሀገር በሚርቅ ጊዜ ክብሯን፣ ገንዘቡን እና ቤቱን በስርአት መጠበቅ አለባት / በዚህ ነገር ላይ ፈፅሞ ክህደት ልትፈፅምበት አይገባም

10. ሁሌም ጥሩ ጠረን ሽታ ሊኖራት ይገባል

11. አፏንና ጥርሶችዋን ሁሌም በሲዋክ ልትቆጣጠር ይገባል

12. እርሱ ፊት ሁሌም በቻለችው አቅም ውብ ሁና ልትገኝ ይገባል

13. ሀሜትን በጣም ልትጠነቀቅ ይገባል / ከርሱም ርቃ ልትቀመጥ አይገባም

14. ቤተሰቡንና የቅርብ ዘመዶቹን ልታከብርለት ይገባል

15. እርሱ የሚውልላትን ጥቂት ነገር ልክ ትልቅ ውሌታ እንደዋለላት አድርጋ ልትቆጥር ይገባል ።

ምንጭ፦ ኪታቡል ከባኢር (66/1)

Send as a message
Share on my page
Share in the group