Translation is not possible.

#ramadan_18

#ረመደን_18

#አንድነት ኃይል ነው !!!!

" አንድነት ኃይል ነው። በአላህ መንገድ ላይ አንድ መሆን የጥንካሬ ሁሉ ምንጭ ነው። በአላህ ዲን ላይ በአንድነት መንቀሳቀስ ብርታት ነው። የአላህን ዲን በአንድነት የጨበጡ ህዝቦች አሸናፊ፣ የበላይ እና የተከበሩ ናቸው።

በትክክለኛ ተውሂድና የሰለፎች መንገድ ላይ መንገዳቸውን ያደረጉ ህዝቦች ለውድቀት አይዳረጉም። ሁሌም የአላህ እርዳታን ይቸራሉ። በሁለቱም ሀገር የስኬት ባለቤቶችም እነርሱ ናቸው።

መበታተን፣ #መጨቃጨቅ : ለሽንፈት ይዳርጋል፣ ኃይልን እንዲላላ ያደርጋል።የተበታተኑ ህዝቦች አንድ መሆን የተሳነው ኡማ ከድል ይርቃል። የሌላው መጫወቻና መሳለቂያ መሆኑ የማይቀር ነው።

አህባቢ ከሁሉም በላይ አንድነት ትብብር ለኛ ወሳኙ ነገር ነውና ወደ አንድነት እንምጣ። አንድነት ሊገኝ የሚችለው ደግሞ ሁላችንም ወደ ቁርዓን ፣ ሐዲስ እና ትክክለኛ የሰለፎችን መንገድ በመከተል ነውና ተውሂድን የረሱልን መንገድ አጥብቀን እንያዝ። ያለ ተውሂድ የረሱል ሰ.ዐ.ወ ሱና አንድነትን ማሰብ ዘበት ነው። መቼም የማይሆን ጉዳይ ነው። ያለፈው ትውልድ እንደዚያ እንደ ግንብ ጠንካራ የአንድነት ባለቤት መሆን የቻለው ጥርት ያለውን ተውሂድ በመያዛቸው ነው ትክክለኛ የአላህ ባርነትን በማሳየታቸው ነው። ስለዚህ እኛም አንድ ልንሆን የነርሱን ፈለግ ልንከተል ይገባል። ያኔ ለጠላት አስፈሪ በማንም የማይዳፈር ምንም የማይፈራ ህዝቦች እንሆናለን።

አንድነትን አደራ. !!!!

"ሁሌም መልካም ሰው ለመሆን እንጣር !!!"

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group