ዚክርና ጥቅሞቹ
🕯አላህን ማሥታወሥ ያለዉ ጥቅም እና ትሩፋት
🔸አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል የመቀዳጃ ትልቅ በር ነው
🔹 ወደ አላህ ሡብሀነ ወተዓላ መዳረሻ መንገድ ነው
🔸 አላህ ሡብሀነ ወተዓላ የዚክርን በር የከፈተለት ሰው የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል
🔹የዚክር በር የተዘጋበት ሰው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል
🔸ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ያገራለት ሠው ዒባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል
🔹ዚክር የከበደውና ከዚክር የሠነፈ ሰው ከዒባዳዎችም ይሠንፋል
🔸 ዚክር ማብዛት ሸይጧንን ከሰው ልጆች ያርቃል
🔹ዚክር አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ያሥደሥታል፣የአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል
🔸በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል
🔹ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል ከአላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ ቅጣትም ይጠብቃል
🔸 ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል
🔹የቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨትም ያድናል
🔸ጀነት ላይ የሰው ልጆች አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በሚያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡
🔹የህሊናን እረፍት ይሠጣል
🔸ዚክር የሚል ሰው ላይ የአላህ ራህመት ይወርድበታል፣ መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል
🔹 በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሰው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፣
ቀብር ውስጥም አላህ ብርሃንን ይፈጥርለታል፡፡
🔸የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሲራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፣ ፊቱም ያበራል፡፡✨ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲያበዙ በተለያዩ የቁርኣን አያዎች (አንቀፆች) ያዘዛቸው፣ ረሡልም ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፣ ዚክር የሚያበዙ ሰዎች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፣
🚩አላህ ሡብሀነ ወተዓላ በቁርኣኑ
يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
(ሡረቱል አህዛብ፡41-42)
[ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :—አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"] ይላል
🚩በሌላውም የቁርአን አያ የሡን ትክክለኛ ባሮችን መገለጫ ሢገልፅ
እነዚያ ያመኑ አላህን በማሥታወሣቸው ልባቸዉ ይረጋጋል የሠው ልጆች ሆይ አላህን በማሥታወሥ የልብ ሠላም እና እርጋታ ይገኛል፡፡ብሏል ፣
🚩በሌላኛው የቁርኣን አያም "አሥታውሡኝ አሥታውሣችኋ
ለሁ "ብሏል፡፡
ሐጅ ሥርአት ላይ ዒባዳችሁን ሥትጨርሡ አላህ ሡብሀነ ወተአላ አሥታውሡ ቤተሠቦቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ከምታሥታውሡት የበለጠ ይላል "
"አላህን ሡብሀነ ወተዓላ በብዛት አሥታውሡት ፣እነሆ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ትድናላችሁ" ይላል
🔸በተለያዩ የቁርኣን አያዎች ላይ የዚክርን ጥቅሞች አላህ ገልጿል።
📎ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሚከተለውን ብለዋል("አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ባሮቹ ላይ ማንኛውንም አይነት ዒባዳ አልደነገገም ዒባዳው በግልፅ በውል የሚታወቅ ገደብና መጠን ቢያደርግለት እንጂ!" )
▶ይህን ዒባዳ የታዘዙ እና የተደነገገላቸው ሰዎችን ኡዝር ባላቸው ሠአት ይህን ዒባዳ ቢተውት ምንም ችግር የለውም ብሎም ቢያሣውቅ እንጂ ፡፡ ዚክር ሢቀር 👌
📌ዚክርን በተመለከተ ይሄን ያህል ብቻ ዚክር አድርጉ ብሎ አላህ አልገደበውም ፣እንዲሁ ዚክርን መተውም አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ለማንም አልፈቀደም ለመተዉም ኡዝር አልሰጠም። አእምሮውን የሣተ፣ ራሡን መቆጣጠር ያቃተው ሰው ካልሆነ በሥተቀር ዚክርን ለመተው አላህ ለማንም ኡዝር አልሠጠም፡፡
እንዲሁም ዚክርንም በዚህ ሠአት በሉ ብሎ አላህ አልገደባቸውም፡፡በጊዜ የተገደቡ ዚክሮች ቢኖሩም በዛ ወቅት እነዚህ ዚክሮች መባል አለባቸው በዚህ ሠአት ቢባሉ ይመረጣል ፣በማለት ነብያችን ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም የተናገሩት ካልሆነ በስተቀር! እንጂ ከዚህ ሠአት ውጭ አላህን ማሥታወሥ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡
ቆማችሁም፣ተቀምጣችሁም ተኝታችሁም አላህን አሥታውሡ፡፡ቀንም ሌሊትም ባህርም ውስጥ የብሥም
ላይ አላህን አሥታውሡ፣ bሀገርም ላይ ይሁን መንገድ ላይ ፣በድንጋጤና በሀዘንም ሆነ በደሥታ ጊዜ በህመምም ሆነ በጤንነት ጊዜ አላህን አሥታውሡ! በገሀድም በሚሥጥርም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆኑ አላህን አሥታው ሱ meb
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.