Translation is not possible.

የጁሙአ ቀን ደረጃ ( ابن القيم)

➛🔘ኢብኑል ቀይም አል ጀዉዚያህ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

⓵« የጁምዓ ቀን ተመላላሽ ባዕል ነው አይሁዳንና ነሷራን ለመቃረንና በዚህ ቀን የተለዩ በሆኑ ኢባዳዎች ላይ እንዲጠነክር ሲባል ብቻውን መፆም ሀራም ይሆናል።

⓶«የጁምአ ቀን በጀነት አሏህ ለጀነት ሰወች ግልፅ የሚሆንበት ቀን ነው።

قال تعالي

አሏህ እንዲህ አለ፦

ﻭَﻟَﺪَﻳْﻨَﺎ ﻣَﺰِﻳﺪٌ

ከኛ ጋ ጭማሬ አለ

‏ﻗﺎﻝ ﺃﻧﺲ - ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ

አነስ ረዲየሏሁ አንሁ ይህን አንቀፅ በተመለከተ እንዲህ አለ፦

ﻳﺘﺠﻠﻰ ﻟﻬﻢ ﻓﻲ ﻛﻞ ﺟﻤﻌﺔ

(በየ ጁምአ ቀን ለጀነት ሰወች አሏህ ይገለጠላቸዋል)

⓷« የጁምዓህ ቀን ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ነው።

قال ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ وعلى آله وصحبه وسلم

ﺧﻴﺮ ﻳﻮﻡ ﻃﻠﻌﺖ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺸﻤﺲ ﻳﻮﻡ

ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ‏[ ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ‏]

የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦

ፀሀይ የወጣችበት ከሆነ ቀን ሁሉ በላጩ ቀን ማለት የጁምአህ ቀን ነው።

📚[[ሙስሊም ዘግበውታል]]

⓸«በጁምአህ ቀን ዉስጥ አሏህ ተለምኖባት የማይመልስባት ሰአት አለች።

ﻗﺎﻝ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ وعلى آله وصحبه وسلم

ﻓﻴﻪ ﺳﺎﻋﺔ ﻻ ﻳﻮﺍﻓﻘﻬﺎ ﻋﺒﺪ ﻣﺴﻠﻢ

ﻭﻫﻮ ﻗﺎﺋﻢ ﻳُﺼﻠﻲ ﻳﺴﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﺷﻴﺌﺎً ﺇﻻ

ﺃﻋﻄﺎﻩ ﺇﻳﺎﻩ

[ ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ ﻭﻣﺴﻠﻢ‏]

የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንዲህ ብለዋል፦

በጁምአህ ቀን ውስጥ የሆነች ግዜ አለች አንድ ሙስሊም የሆነ ባሪያ ቁሞ እየሰገደ እና አሏህን እየለመነ አያገኛትም የለመነውን ነገር አሏህ ቢሰጠው እንጂ።

📚[[ቡኻሪና መስሊም ዘግበውታል]]

⓹«የጁምአህ ቀን ትንሳኤ ቀን የምትቆምበት ቀን ነው።

قال ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ

ﻭﻻ ﺗﻘﻮﻡ ﺍﻟﺴﺎﻋﺔ ﺇﻻ ﻓﻲ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ‏

[ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ‏]

መልእክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

ትንሳኤ ቀን ጁምአህ ቀን እንጂ አትቆምም።

📚[[ሙስሊም ዘግበውታል]]

⓺«የጁምአህ ቀን ወንጀሎች የሚታበሱበት ቀን ነው።

⓻«በጁምአህ ቀን የሞተ ሰው መጨረሻው ያማረ መሆኑን ያሳያል።

قال ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ

ﻣﻦ ﻣﺎﺕ ﻳﻮﻡ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ﺃﻭ ﻟﻴﻠﺔ

ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ﻭُﻗِﻲَ ﻓﺘﻨﺔ ﺍﻟﻘﺒﺮ

[ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ‏]

የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦

የጁምአህ ቀን ወይም ለሊት የሞተ ሰው ከቀብር ፈተና ተጠበቀ ።

📚[[ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል]]

⓵«የጁምአህ ቀን ሰደቃ ከሌላው ቀን ሰደቃ እጅግ በጣም ምንዳዉ ይደራረባል።

ﻗﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴﻢ

ﻭﺷﺎﻫﺪﺕُ ﺷﻴﺦ ﺍﻹﺳﻼﻡ ﺍﺑﻦ ﺗﻴﻤﻴﺔ ﺇﺫﺍ ﺧﺮﺝ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺠﻤﻌﺔ ﻳﺄﺧﺬ

ﻣﺎ ﻭﺟﺪ ﻓﻲ ﺍﻟﺒﻴﺖ ﺧﺒﺰ ﺃﻭ ﻏﻴﺮﻩ ﻓﻴﺘﺼﺪﻕﺑﻪ

ﻓﻲ ﻃﺮﻳﻘﻪ ﺳﺮﺍً

ኢብኑል ቀይም አሏህ ይዘንላቸውና ኢብኑ ተይምያ ወደ ጁምአህ ሲወጡ እቤት ያገኙትን ዳቦም ሆነ ሌላ ነገር ይይዙና በመንገዳቸው በሚስጥር ሲሶድቁት አይቻለሁ ይላሉ።

አሏህ በጁምዓህ ቀን ከሚጠቀሙ የአሏህ ባሮች ያድርገን።"

🍃🍃 መልካም ጁመአ እህት ወንድሞቼ🍃

Send as a message
Share on my page
Share in the group