ትንሽ ስለ ዱኒያ ነክ ጉዳይ እናውራ‼
=========================
✍ ሌላ ጊዜ በሰፊው የምመለስበት ቢሆንም ሰሞኑን የተነገሩ ሁለት ዜናዎችን ሰምታችኋል ኣ?
1) በሃገራችን በገመድ ላይ ተንጠልጣይ የህዝብ ትራንስፖርት (Cable Car) ሊጀመር ነው ተብሏል። አስበው! ጠዋት ጠዋት ጦር ኃይሎች፣ ስቴዲየምና መሰል ቦታዎች ላይ ያለው መዘጋጋት! የግል መኪና ቢኖርህ እንኳ ዘለህ መሄድ አትችልም። ኬብል ካር ሲጀመር ግን ተዘጋግተው እንደ ዔሊ የሚሄዱትን መኪኖች ዝቅዝቅ እያየህ እየሳቅክ ታልፋቸዋለህ። ስጋቱ እንዳለ ሆኖ!
*
②) ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌብር ተጨማሪ የክፍያ አማራጭ እንዲሆን የ POS ማሽኖችን የሙከራ ሥራ ጀምሯል። ቴሌብር አንድ ቀን የባንኮችን ሥራ መሥራት ከጀመረ የሚያመጣውን አስገራሚ ጫና የሆነ ጊዜ ጽፌ ነበር። ባንኮች እንደት እንደሚቋቋሙት አላውቅም።
እንዲህ አይነት የመንግስት ተቋማት በብዙ የክፍያ አማራጮች ላይ ሳይቀር ሳትወድ በግድ እንድትጠቀማቸው ትገደዳለህ።
ለምሳሌ፦ ተሌብርን ለመብራት ክፍያ፣ ለአውሮፕላን ትኬት ክፍያ፣ ለነዳጅ ክፍያ፣ ለትምህርት ክፍያ፣ ለግብር ክፍያ፣ ለማንኛውም ንግድ ግብይት… ወዘተ። በእንዲህ አይነት ሁኔታ የዘምዘምና ሂጅራ ባንኮች ዋና ኃላፊውም ቢሆን በራሱ ባንኮች መክፈል ቢፈልግም ሁኔታው ስለሚያስገድደው የግድ ይጠቀመዋል።
★
√ አሁን ኬብል ካርን እኛ ሃገር ላይ ማን ያስበዋል?
ሃሳቡኮ አዲስ የቢዝነስ ሃሳብ አይደለም። ገና በ20ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ የጀመረ ነው። ግን ወዳጄ! እኛ ሃገር አይገባም እያልክ መሞኘትህን ተው። አቅም ያለው ያስገባዋል።
ቀስ በቀስ የአማዞንና የአሊባባ ኢኮመርስ ሥራ እኛ ሃገር ሲገባስ? መርካቶ decentralized ሲደረግስ?
ያዘዝኩት እቃ በፋብሪካ ዋጋ ቤቴ በር ድረስ እየነጣልኝ፤ የእናቴ ልጅ ብትሆን እንኳ 5 ኪሎ ሜትር መንገድ ተጉዤ ካንተ አልገዛም።
ገባህ አባባሌ!
ካልገባህ ሌላ ጊዜ እመከስና እስኪገባህ እነግርሃለሁ።
ነቃ በል! ከቴክኖሎጂው ጋር ዘምን!
የሆነ ነገር ስልህ ይሄ በኛ እድሜ እኛ ሃገር አይመጣም አትበል። እንደ ኬብል ካር አቅም ያለው ያመጣውና ሳትወድ በግድ ከገበያው ያስወጣሃል።
||
t.me/MuradTadesse