የኛ ነገር ... ከሐላል እየፆምን በሐራም እናፈጥራለን!

~

ፆማችንን ከሐራም ነገሮች እንጠብቅ። ግብይታችን በየትኛውም መልኩ ከሰው ሐቅ ጋር እንዳይነካካ እንጠንቀቅ። አይናችንን ካልተፈቀደ አካል እንስበር። ስልኮቻችንን ወደ ሐራም እንዳያደርሱን እንቆጣጠር። በረመዷን ከሰው ጋር ያለንን ቅልቅል እንቀንስ። በተለይ ደግሞ የምላሳችንን ነገር እናስብበት። ፆማችን አጉል መርራብ እና መጥጠማት እንዳይሆን እንጠንቀቅ።

ታላቁ ታቢዒይ የሐያ ብኑ አቢ ከሢር ረሒመሁላህ ፆመኛ ሆኖ ሃሜትና ነገር ማሳበቅ ላይ ስለሚሰማራ አካል እንዲህ ይላሉ፦

"ሰው ንፁህ ከሆነ ሐላል (ምግብና መጠጥ) እየፆመ ቆሻሻ በሆነ ሐራም - በወንድሙ ስጋ - (በሃሜትና ነገር ማሳበቅ) ያፈጥራል።"

ምንጭ ፦ [አልሒልያህ፣ አቡ ኑዐይም፡ 3/69]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ

=

የቴሌግራም ቻናል፡-

https://t.me/IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

Telegram: Contact @IbnuMunewor

كناشة ابن منور
Send as a message
Share on my page
Share in the group