Tidak bisa diterjemahkan.

የሚላስ የሚቀመስ ፍለጋ ነበር ከመጠለያ ካምፑ የወጣው። ሁለት ቀናት እህል ያልቀመሱ ቤተሰቦቹን አንጀት ሊያርስ ሲከንፍ እየበረረ እርዳታ ከሚወረወርበት ቦታ ደረሰ።

ከሰማይ ወድቆ መሬት የተበታተነውን ዱቄት እንደነገሩ ከነቆሻሻው በፌስታል ሰብስቦ ወደ ቤተሰቦቹ ተመለሰ። አብስለው ሊመገቡት፣ ጋግረው ሊያፈጥሩበት እየቋመጠ ወደ መጠለያ ካምፑ ሮጠ።

ግና ያየው ነገር የሰበሰበውን እንዲበትን አስገደደው። በቆመበት ደርቆ ቀረ። ቤተሰቦቹ ሁሉም በወራሪዋ ጥቃት ተመተው ከመሬቱ ወድቀዋል። እንደራባቸው አላህን ተገናኝተዋል። ጋሻ መከታውን አጥቶ በለጋ እድሜው ብቻውን ቀረ። ያለ ዘመድ አዝማድ ህይወቱን እንዲገፋ የአላህ ውሳኔ ሆነ። ግንቡን እንደተደገፈ ተንሰቅስቆ አለቀሰ።

ያለ ሱሁር የሚጾሙ ያለ ምግብ የሚያፈጥሩ በደም በተጨመላለቀ ቁርኣን የሚቀሩ ወንድሞቻችሁን አትዘንጓቸው። በዱዓ ዘወትር አስታውሷቸው።

Kirim sebagai pesan
Bagikan di halaman saya
Bagikan di grup