Translation is not possible.

"አፍጥርም ሱሑርም በውሀ አልሀምዱሊላህ" ይህ የጋዛዊያኑ ድምፅ ነው። በባዶ ሆዳቸው ውሀ ብቻ እየተጎነጩ ተከታታይ ቀናትን ከሚፆሙት ወንድሞች መሐል የተሰማ ልብን ሰርስሮ፣ የዕንባን ቋጠሮ የሚበጥስ ድምፅ!

በምግብ እጦት የተቃጠለ አንጀታቸውን በውሃ አርጥበው መልሰው ራሳቸውን ለፆም ያዘጋጃሉ። ተሻምተው የደረሰው ቂጣ ሲመገብ ዕድሉን ያላገኘው ባዶ ሳህን ይዞ ወደ ቤቱ ይመለሳል። አንጀቱን በውሀ አረስርሶ በባዶ ሆዱ ያድራል። ሩህማከ ያ አላህ

4 views
Send as a message
Share on my page
Share in the group