Тарҷума мумкин нест.

በረመዳን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች

~~~~

① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣

② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር ሳይሰግዱ መተኛት፣

③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣

④ ረመዳንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣

⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣

⑥ ተራዊሕ ላይ በየ አራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣

⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና ጊዜ መስጠት፣

⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው)

⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ " እያሉ በእስፒከር መጮህ፣

(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣

(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣

(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣

(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣

(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣

(15) ሴቶች ሽቶ ተቀብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣

(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣

(17) ሃሜት፣

(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣

(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ፣ ወዘተ ማሳለፍ፣

(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣

(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣

(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርአን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)

(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣

(24) አንዳንድ አካባቢዎች ዒሻን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣

(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣

(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማዘዝ፣ ወዘተ

=ዒብኑ ሙነወር

Send as a message
Share on my page
Share in the group