Translation is not possible.

እንደሆነ ይረዳበታል። ይህም የሚሆነው ግለሰቡ የፈለገውን እና የተፈቀድልትን መብላት እና መጠጣት እንዲሁም ከተፈቀደለት አካል ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ በፈለገ ሰአት እንዲያገኝ አላህ ያገራለት መሆኑን ስለሚያስተውልበት ነው። ስለሆነም ጌታውን ያመሰግናል፣ ይህንን ማግኘት ያልቻለውን ድሃ ወንድሙን ያስታውሳል በዚህም የተነሳ ለሱ ምፅዋትን (ሰደቃን) ይሰጣል እንዲሁም መልካም ተግባራትን በመፈፀም የቸርነትን ባህሪ ይላበሳል።

ከፆም መደንገግ ጥበቦች መካከል፦ የሰው ልጅ እንዴት አድርጎ ነፍሱን (ስሜቱን) መቆጣጠር እና ሙሉ ለሙሉ በርሱ የበላይነት ስር በማዋል ለርሶ በቅርቢቱ ዓለምም (ዱንያ)ም ይሁን በወዲያኛው ዓለም (አኼራ) መልካም እንዲሁም ስኬታማ ወደ ሆነው አቅጣጫ መምራት እንደሚችል የሚለማመድበት መድረክ መሆኑ ነው። በዚህም ነፍሱን ከፍላጎቶቿ መከልከል የማይችል እንስሳዊነት የተጠናወተው ሰብአዊ ፍጡር ከመሆን ይልቅ ለርሷ ጠቃሚ የሆነውን ወደ ማሟላቱ ያዘነብላል።

ከፆም መደንገግ ጥበቦች መካከል፦ ፆመኛ ምግብን በመቀነሱ የተነሳ ጨጓራ እና መሰል የምግብ መፈጨት ሂደት የሚከናወንባቸው የሰውነት ክፍሎች ለተወሰነ ግዜ እረፍት ያገኛሉ በተጨማሪም አንዳንድ ለሰውነት አላስፈላጊ የሆኑ በሰውነት ውስጥ የሚገኙ እንደ ስብ እና መሰል ትርፍ ጎጂ ነገሮች መወገድ ከጤና ጋር ተያያዥነት ካላቸው የፆም ጥቅሞች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ኢንሻ አላህ ክፍል ሶስት ይቀጥላል…

በበሸታ እና በመንገድ ላይ ስላሉ ሰዎች የጾም ህግጋት በተመለከተ ይሆናል። 

አላህ በተሞላ ጤንነት እና እሱ በሚወደው መልኩ ረመዷንን ከሚጾሙት ያድርገን። በተለያየ የጤና እክል ላይ ላሉትም አላህ ጤንነትን ይስጣቸው!!

✍️መንቁል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group