Tarjima qilib boʻlmadi.

"ህያዋን ከሚቀበሩበት ከኦፈር ማረሚያ ቤት ወንድሞቻችሁ የተላለፈ መልዕክት" ይላል ደብዳቤው መልዕክቱን ሲጀምር። ትኩረት ሰጥተህ ስታነበው ራስህን ትንቃለህ። አንገትህን ነቅንቀህ ትገረማለህ። አቀርቅረህ ታነባለህ። እኔስ ብለህ ራስህን ትገመግማለህ።

"መልካም ሰላምታችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ። ስለ ሁኔታችን አናወጋችሁም። በህይወት ያለን ሙታን መሆናችንን መንገራችን በቂ ነው"

"አናስቸግራችሁም ከባድ ነገርም አንጠይቃችሁነረ አንድ ነገር ብቻ! እርሱም አይከብዳችሁም ብለን ተስፋ እናደርጋለን። አሳሪዎቻችን እስር ቤት ውስጥ የሰላትን ወቅት አዛብተውብናልና ከቤታችሁ ድምፅ ማስተጋቢያ ተጠቅማችሁ የአዛን ድምፅ አሰሙን። አሊያም ሞንታርቦ በአቅራቢያችን ትከሉ። ለሊትና ቀኑን መለየት ተስኖናል። አዛን እንዳንልም ከልክለውናል። ወዳጆቻችን ሆይ የሰላትን ወቅት መለየት ተስኖናል" ይላል።

የስቃይ እቶን እየዘነበባቸው ለጌታቸው የሚያቀርቡት ምክንያት ኖሯቸው አላህ አላህ እንድንል የሰላት ወቅትን ጠቁሙን ይላሉ። መርሀቸው አንድ ነው። ለአላህ እንጂ ለማንም አናጎነብስም ከእርሱ ውጪም ለማንም ግንባራችንን መሬት አንደፋም ይላል ሊሳነል ሐላቸው። ያለምንም ምክንያት ሰላትህን የተውከው ወንድሜ ተመከርበት! የአዛን ድምፅ የሰለቸሽ እህቴ ተገሰጪበት!

image
Xabar sifatida yuborish
Sahifamda baham ko'rish
Guruhda ulashish