ጥቂት እውነታዎች ስለ ረመዷን

~

1- የረመዷን ወር ፆም ከኢስላም አምስቱ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ምሰሶ ነው።

2- ረመዷን በኢስላማዊው አቆጣጠር 9ኛው ወር ነው።

3- የረመዷን ወር ፆም የተደነገገው በ2ኛው አመተ ሂጅራ ነው። ነብያችን ﷺ ባጠቃላይ የፆሙት 9 ረመዷን ነው።

4- ረመዷን ቁርኣን የወረደበት ወር ነው።

5- ልዩ የሆነችዋ ለይለተል ቀድር የምትገኘው በረመዷን ወር ውስጥ ነው።

6- በረመዷን የተፈፀመ ዑምራ የሐጅ ደረጃ ወይም ከነብያችን ﷺ ጋር የተፈፀመ ሐጅ ደረጃ አለው።

7- ረመዷን የጀነት በሮች የሚከፋፈቱበት፣ የጀሃነም በሮች የሚዘጋጉበት፣ ሸይጧኖች የሚጠፈሩበት ወር ነው።

8- የረመዷን ወር ከኢዕቲካፍ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።

9- ረመዷን እንደ የበድር ድል፣ የመካ መከፈት፣ የቃዲሲያ ድል፣ የዑዛ ጣኦት መወገድ፣ ሞንጎሎች የተሸነፉበት የዐይን ጃሉት ድል፣ ወዘተ ትልልቅ ክስተቶች የተከሰቱበት ወር ነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group