Translation is not possible.

🌙

     የረመዷን ዝሆኖች ተጠንቀቁ!!

  ኢማሙ ማሊክ አላህ ይዘንላቸው መስጂድ አል_ነበዊ ውስጥ ተቀምጠው የረሱልﷺ  ሐዲስ ያስተምሩ ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን በማስተማር ላይ ሳሉ አንዱ ድምፁን ከፍ አድርጎ

  "መዲና ውስጥ ዝሆን ገብቷል… መዲና ውስጥ ዝሆን መጥቷል"

እያለ ይጮሃል።

ጩኸቱን የሰሙ ተማሪዎች ከአንዱ በስተቀር ሁሉም እየሮጡ ዝሆኑን ለማየት ወጡ። ምክንያቱም ከዝያ ቀን በፊት ዝሆን አይተው አያውቁም ስለ ነበር አጓጓቸው።

  ሁሉም ሲወጡ ብቻውን የቀረው

የሕያ ኢብኑ የሕያ አል_ለይሲ ነበር።

ኢማሙ ማሊክ: 

   "ለምን አብረሃቸው አልወጣህም?"

ብለው ጠየቁት;

የሕያ:

  "ኢማም ሆይ! እኔ ወደ መዲና የመጣሁት ማሊክን ለመገናኘት እንጂ ዝሆን ለማየት አይደለም።"

ሲል መለሰላቸው።

  እንደ ሚታወቀው የኢማሙ ማሊክ ሙወጣእ ከየሕያ ኢብኑ የሕያ አል_ለይሲ በኩል የተላለፈው ጠንካራው እና ተመራጩ ነው።

እናም ወዳጄ………

   ረመዷን ላይ የሚመጡ ብዙ ዝሆኖች አሉ።

ሩጠው እንደ ወጡ ብዙ ተማሪዎች አላማውን የረሳ ዝሆኖች እያየ ረመዷን ሲያመልጠው; ከረመዷን መቅሰም ያለበትን የሚያውቅ የሆነ ሰው ዝሆኖች በማየት ረመዷኑን አያስመልጥም።

  በእርግጥም በአራት እግሩ የሚሄድ ግዙፍ ዝሆን ላይመጣ ይችላል፦

ግን…………

💫በረመዷን የሚለቀቁ ተከታታይ ፊልምና ድራማዎች;

💫የብልሽት መናኸሪያ የሆኑ የብዙኋን መገናኛዎች;

💫ነሺዳ እና መንዙማዎች;

💫በስርዓት ያልገደብከው እጅህ ላይ ያለው ስልክህ;

💫የረመዷን ትርጉምና አላማ ያልገባቸው ጓደኞችህ;

:

:

:

:

    እና የመሳሰሉ ብዙ የረመዷን ዝሆኖች አሉ።

🚫አውቀህ ተ ጠ ን ቀ ቃ ቸ ው!!

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group