🔻 አቡ ዑበይዳ

ዛሬ የአልቃሳም ብርጌድ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ ለጽዮናዊው አካል አስደንጋጭ መልእክት አስተላልፈዋል፡- የኔታንያሁ የቅርብ ጓደኛን ጨምሮ 7 ተጨማሪ የጽዮናውያን እስረኞች በጋዛ በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ተገድለዋል።

በዚህ መስረት በጋዛ ውስጥ ከቀሩት 134 እስረኞች መካከል 70ዎቹ ሆነ ተብሎ በእስራኤል ጥቃት ተገድለው ሊሆን ይችላል። ከፍልስጤም ውጭ ድርድር እየተካሄደ ባለበት ሰአት ተቃውሞው ግማሹ እስረኞች በወራሪው እጅ እንደተገደሉ እና አገዛዙ ለሕይወታቸው ምንም ደንታ እንደሌለው ለጠላት ለመንገር ወደ ፊት ቀርቦ የሟቾችን ስም እንኳ ሳይቀር ይፋ አድርጓል። ይህ መረጁ ለሰፋሪው መንግስት፣ ለህዝቡ እና ለተደራዳሪው ልዑካን ቡድን ይፋ የሆነው የእስረኛ ልውውጡን ለማድረግ ሐማስ በህይወት ያሉ እስረኞችን ስም እንዲያቀርብ በአደራዳሪዎች አማካይነት እስራኤል ከጠየቀች በኋላ ነው።

አቡ ዑበይዳ ይህንን መረጃ ሲገልጽ “ለአምስት እስረኞች የምንጠይቀው ዋጋ ለአሥር እስረኞች ወይም ለሁሉም እስረኞች የምንጠይቀውን ዋጋ ተመሳሳይ ነው” በማለት ሁለም ለሁሉም የሚለውን ጥያቄውን በድጋሚ ተናግሯል። ሁሉም የፍልስጤም እስረኞች ነፃነትን የመጠየቅ የተቃውሞው አቋም እንዳልተለወጠ አረጋግጧል።

እነዚህ ጀግኖች ተዋጊዎች ታጋቾችን ብቻ ሳይሆን የመላው የፍልስጤም እስረኞችን ነፃነት እየጠበቁ ስለነበር የበርካታ የአልቃሳም ተዋጊዎች ሰማዕትነት በመልእክቱ ውስጥ መጠቀሱ ሊደበቅ አይገባም ብሏል።

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group