Табасаранан алхьа кха дац.

#ተውሒድ_የመዳኛ_መንገድ_ነው

========================

↪️ከኢብኑ ዐባስ ተይዞ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ በጭንቅ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር:–

( لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ الْعَظِيمُ الْحَلِيمُ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ رَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ، لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَرَبُّ الْأَرْضِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ ) متفق عليه

“ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም! እርሱም ሀያልና ቻይ ነው። ከአንድ አላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም! እርሱም የሰማያትና የምድር እንዲሁም የዐርሽ ጌታ ነው።” ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

↪️ከአቢ በክር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ የጭንቀተኛ ሰው ዱዓ የሚከተለው ነው ብለዋል:–

( اللَّهُمَّ رَحْمَتَكَ أَرْجُو ، فَلَا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ ، وَأَصْلِحْ لِي شَأْنِي كُلَّهُ، لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ ) حسنه الألباني في صحيح أبي داود

“አላህ ሆይ! እዝነትህን እከጅላለሁ፣ ራሴን ለራሴ የአይን እርግብግብታ ያህል እንኳን አትተወኝ፣ ጉዳዬን ሁሉ አስተካክልልኝ፣ ከአንተ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም!።” አልባኒ አቢዳውድ ላይ ሀሰን ነው ብለውታል።

↪️ከሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ ተይዞ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ:–

دَعْوَةُ ذِي النُّونِ إِذْ دَعَا، وَهُوَ فِي بَطْنِ الْحُوتِ : ( لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ ؛ فَإِنَّهُ لَمْ يَدْعُ بِهَا رَجُلٌ مُسْلِمٌ فِي شَيْءٍ قَطُّ إِلَّا اسْتَجَابَ اللَّهُ لَهُ ) صححه الألباني في صحيح الترمذي

“የአሳው ባለቤት "ነቢዩላህ ዩኑስ" ጥሪ (ዱዓ) በአሳው ሆድ ውስጥ ሆኑ የሚከተለው ነበር «ከአንተ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም! ጥራት ይገባህ እኔ ከበደለኞች ሆኜ ነበር» በዚህች ቃል ሙስሊም የሆነ ሰው አላህን አንዳች ነገር አይለምንባትም አላህ ልመናውን ቢቀበለው እንጂ።” አልባኒ ትርሚዚይ ላይ ሶሂህ ነው ብለዋል።

↪️ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ትላለች: ነቢዩ ﷺ ቤተሰባቸውን ሰበሰቡና የሚከተለውን አሉ:–

أَنَّ النَّبِيَّ

صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ جَمَعَ أَهْلَ بَيْتِـهِ ، فَقَالَ : ( إِذَا أَصَابَ أَحَدَكُمْ غَمٌّ أَوْ كَرْبٌ ، فَلْيَقُلِ : اللَّهُ اللَّهُ رَبِّي ، لَا أُشْرِكُ بِهِ شَيْئًا )صححه الألباني في السلسلة الصحيحة

“አንዳችሁን ጭንቀት ከገጠማችሁ: አላህ ጌታዬ ነው በርሱም ምንም አላጋራበትም ይበል።” አልባኒ በሲልሲለቱ ሶሂሃ ሰሂህ ነው ብለውታል።

✔️ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ:– (ይህቺ በባሮቹ ላይ የአላህ ሱና ናት፣ የዱንያ አስቸጋሪ ጭንቀት ሁሉ አልተመለሰችም በተውሒድ ቢሆን እንጂ፣ ለዚያም ነው የጭንቀት ጊዜ ዱዓ በተውሒድ ቃል የሆነችው፣ የአሳው ባለቤት "ነቢዩላህ ዩኑስ" የተጨነቀ ሆኖ አላህን አለመነባትም አላህ ጭንቀቱን በተውዷ ቃል ቢገላግለው እንጂ፣ ከባድ በሆነ ጭንቀት ውስጥ ሽርክ እንጂ አይጥልም፣ ከርሷም የሚያድን የለም ተውሒድ እንጂ፣ እሱ የፍጡራን አስደንጋጭና መውጫው መጠበቂያውና መርጃው ነው።) አልፈዋኢድ ሊብኒል ቀይም 67

ተውሒድ የዱኒያም የአኼራም የጭንቀት ጊዜ መውጫ ነው።

✍🏻ኢብን ሽፋ ሙሀረም 17/1440

========================

Send as a message
Share on my page
Share in the group