Translation is not possible.

ልጁ በትካዜ ተውጧል። ቅስሙ ተሰብሯል። በሃሳብ ሩቅ ተጉዟል። ቀጭን

እንጨት በእጁ ጨብጧል። መሬቱን እየጫረ ስዕል የሚስልበት እንጨት

ነው። አንዲት ሴት በአጠገቡ እያለፈለች ሳለ ተመለከተችው። ሀዘን

እንዳጠላበት አስተዋለች። ሁኔታው ልቧን አራራው። " እዚህ ምን እየሰራህ

ነው የኔ ልጅ? ብላ ጠየቀችው። ልጁም " የጀነትን ስዕል ከሳልኩ በኋላ

ለብዙ ቦታ እከፋፍለዋለሁ" አላት። በልጁ ምላሽ ፈገግ ተሰኘች። በመቀጠል

" ከክፍልፋዮቹ መካከል አንዷን ግንጣይ መውሰድ እችል ከሆነ ዋጋው ስንት

እንደሆነ ትነግረኛለህ?" አለችው። ካቀረቀረበት አንገቱን ቀና አደረገና " አዎ

ይቻላል፤ የምፈልገው 20 ሪያል ብቻ ነው" አላት።

.

.

.

.

.

ሴትዮዋም 20 ሪያል ከጣፋጭ ብስኮቶች ጋር ሰጠችው። ወደ ቤቷ

አመራች። ሌሊት ላይ አስደናቂ ህልም አየች። ራሷን ጀነት ውስጥ

ተመለከተች። ሲነጋ ህልሟን ለባሏ አጫወተችው። በሀዘን ቅስሙ ከተሰበረው

ልጅ ጋር ስለነበራት ውሎ ነገረችው።

.

.

.

.

ይህን አስገራሚ ታሪክ የሰማው ባል ልጁ ወዳለበት አካባቢ ገሰገሰ።

ከሳለው የጀነት ክፍልፋይ አንዷን ክፋይ ለመግዛት ቋመጠ። ልጁ አጠገብ

ደረሰ። ሰላምታ ተለዋወጡ። ከዚያም እንዲህ አወጉ: -

.

.

.

.

ሰውየው " ከጀነት ክፍልፋዮች መካከል አንዷን ቁራጭ መግዛት

ስለምፈልግ ዋጋው ስንት ነው?"

.

.

.

ልጁ " በፍፁም አልሸጥም"

.

.

.

ሰውየው "ትላንት ለባለቤቴ አንዷን ክፋይ በ20 ሪያል አልሸጥክላትምን?

.

.

.

ልጁ "ሚስትህ እኮ 20 ሪያል ያወጣችው የነፍሴን ስብራት ለመጠገን

እንጂ ጀነትን በ20 ሪያል ፈልጋ አይደለም። አንተ ግን ጀነትን በ20 ሪያል ብቻ

ነው የፈለከው። ጀነት እኮ የተተመነ ዋጋ የላትም። ወደጀነት ለመግባት

የብዙዎችን የነፍስ ስብራቶች በመጠገን ወጌሻ መሆን ይጠይቃል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group