Translation is not possible.

🚨 በሞስኮ ውይይት ላይ የሚገኙት የፍልስጤም ቡድኖች፡-

በሞስኮ የተሰባሰቡት የፍልስጤም ቡድኖች ዛሬ ሐሙስ ማለዳ በጋዛ ከተማ በአል ራሺድ ጎዳና ላይ ምግብ ፍለጋ ላይ በነበሩ ከ146 ቀናት በላይ በታወጀባቸው የረሃብ ጦርነት ምክንያት ያለ ምግብ እንዲኖሩ የተደረጉ ንፁሀን ዜጎች ላይ በእስራኤል ወራሪው ኃይሎች የተፈፀመውን እና ከ 104 በላይ የሞቱበትን እና ከ 250 በላይ የቆሰሉበትን ዘግናኝ የጽዮናዊያን ወንጀል አውግዘዋል።

ይህ ወንጀል ኔታንያሁ እና መንግስቱ ህዝባችንን ለመግደል እና ለማንገላታት ማቀዳቸውን የሚያረጋግጥ እና በፍልስጤም ህዝባችን ላይ ከደረሰው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ጋር ተያያዥ ነው፡፡ ለወረራው ፖለቲካዊ ሽፋን እና ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር ኃላፊነት ይወስዳል፡፡

ይህ ወንጀል ወረራ እና ጦርነቱን ለማስቆም ያልቻለውን የዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ውሳኔ ላይም የተቃጣ ጥቃት ነው። ተሰብሳቢዎቹ ይህንን የግድያ ማሽን ለማስቆም የአለም ሀገራት በአስቸኳይ እና በፍጥነት ጣልቃ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በስብሰባ ላይ የሚገኙት የፍልስጤም ቡድኖች "ህዝባችንን ለመከላከል በአንድነት በመቆም ወረራውን ለማስወገድ ብሄራዊ አንድነታችን እንደሚያስፈልግ አበክረን እናሳስባለን" ያሉ ሲሆን ወራሪውን እና የሚደግፉትን የውጭ አካላት በተለይም አሜሪካን ለማስወገድ እና የሕዝባችን የነፃነት እና የሉዓላዊነት ምኞት፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብታቸውን ተጠቅመው አል ቁድስ ዋና ከተማዋ የሆነች ነፃ አገራቸውን የመመስረት ተስፋን እውን ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።

ሐሙስ፡ 19 ሻባን 1445 ዓ.ሂ

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group