Translation is not possible.

"አንዳንድ ጊዜ ህይዎት አንተ እንዳሰብከው አትሄድም፤ አንተ ያሰመርክላትን መስመር አትከተልም።"

ይህም ማለት አንተ ያሰመርከላት የጉዞ መስመር አላህ ካለውና ካሰበልህ በተቃራኒ ነበር ማለት ነው።

ስለዚህ እርሱ ያለው ይፈፀማል።

አላህ ባሮቹን አይበድልምና የርሱ ፍፃሜም በላጩና የተሻለው ይሆናል።

"በስኬት ጎዳና ላይ እያለህ፣ ውድቀት ያጋጥምሃል፤ ሊጠገን ለማይችል 'ለልብ ስብራትም' ይዳርግሃል።"

ለማንኛውም ግን ዱንያ "ዱንያ" ናት፤

አጭር፣ ጠፊና አታላይ የሆነች።

ስለዚህ ብዙም አትጨነቅላት።

ሞተህ ትገላገላታለህ።

ለቀጣዩና ለዘላለማዊው የአኺራ ህይዎት ግን ተጨነቅ፣

በቂ ስንቅንም አዘጋጅ፤ ከስንቆቹም ሁሉ በላጩ "አላህን መፍራት" ነው።

ለነገሮች ሁሉ ተስፋ አትቁረጥ። ወኔህ ሁሉ አይሟጠጥ።

ሰበቡን አድርስ፤ ከዚያም በአላህ ላይ ተመካ።

አልሐምዱሊላህ ዓላ ኩሊ ሐል።

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group