Translation is not possible.

🔻ሶሪያ-እስራኤል!

በሶሪያ ደማስቆ ሁጄይራህ ከተማ እንዲሁም በደማስቆ ዳርቻ ሰይዳ ዘይነብ አካባቢ አቅራቢያ ላይ እስራኤል የአየር ድብደባ ፈፅማለች፡፡ የመጀመርያ ደረጃ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱን እና የእሳት አደጋ መከላከያ ቡድኖች ወደ ስፍራው አቅንተዋል የሚል መረጃ ጋዜጠኛው ዊሳም ኢሳ ይፋ አድርጎ ነበር፡፡

የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መረጃ፡-

"ትላንት ምሽት 3፡35 ላይ የእስራኤል ጠላት በወረራ ያዘችው የጎላን ኮረብታ አቅጣጫ የአየር ጥቃት በደማስቆ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ ፈፅማለች ያለ ሲሆን የሶሪያ አየር መከላከያም ለእስራኤል ጥቃት ሚሳኤሎች ምላሽ በመስጠት አብዛኞቹን ማክሸፍ መቻሉን እና አንዳንድ ቁሳዊ ኪሳራዎች ብቻ መድረሳቸውን አስታውቋል፡፡"

በሙስሊሙ ዓለም የተፈጠሩ ሁሉንም አዳዲስ መረጃዎች በተለይም በወቅታዊ የፍልስጤም ጉዳይ እውነተኛ እና ሚዛናዊ መረጃ ለማግኘት የሙሐመድ ትውልድ ገፅን ፎሎው ያድርጉ

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group