Хьо дакъа дацанаш махь йоьтта.

ሰዎችን ተዋቸው!!

ነገ ግርዶሹ ይነሳል፣ የተደበቁ ነገሮችም በሙሉ ይወጣሉ፣ ምስጥሮችም ይጋለጣሉ።

ወንጀልህን ከምትደብቀው በላይ መልካም ስራህን ደብቅ

ብቻህን እንደተወለድከው ሁሉ የምትሞተውም ብቻህን እንደሆነ እወቅ

ሰዎችን ተዋቸው

አይደለም ላንተ አላህ ከቀደረላቸው ውጪ ለራሳቸውም ምንም ማድረግ አይችሉም

ሁሌም ህያው በሆነው በአርሹ ባለቤት ተመካ

ከጭቃ የተፈጠሩና ነገም ወደዛው የሚመለሱ ደካማ የሰው ልጆችን ተስፋ አታድርግ፣የነርሱ መራቅና መቅረብ መውደድና መጥላታቸውም አንተ ዘንድ እኩል ይሁኑ

ለዲንህና ለዱኒያህ የሚበጅህን ነገር አውቀህ እዛ ላይ ፅና!

ጨለማው ሲወገድ ያለቀሱት ካለቃቀሱት ይለያሉ፣

ለሆዳቸው ብቻ የሚኖሩና ዓላማ ቢስ የሆኑ ሰዎች ካሰቡት ለመድረስ ቀን ከሌሊት ይለፉ የነበሩ ሰዎችን ተሳክቶላቸው ሲያዩ በቁጭት አለንጋ እራሳቸውን ይገርፋሉ

የሙእሚን ግቡ አላህን ማስደሰትና ጀነትን መውረስ ነውና ሳትደርስ የደረሰክ መስሎህ ከመንገድ እንዳትቀር፣

ከወዳጅ ነጥሎ ከሰፊው ቤት አውጥቶ ጨለማና ጠባቡ ጉርጓድ ላይ ወስዶ ሊጥልህ በድንገት የሚመጣውን ሞት ዘወትር በልብህ አስታውስ

በዚህ በጣም ከባድና አስቸጋሪ በሆነው የጘርጘራ ሰዓት ላይና ከዛም በኋላ የሚጠቅምህ ስራህ ነውና መልካም ስራ ላይ በርታ ፣የምትሰራው ስራም ኢኽላስ ይኑረው፣

ሰው ምን ይለኛል ብለህ መልካምን ስራ አትተው፣ ወንጀልንም አትዳፈር

ሰዎችን ተዋቸው!!

(ኡስታዝ አህመድ አደም)

Send as a message
Share on my page
Share in the group