Translation is not possible.

ለዳዕዋ ጥንካሬ ከፊል አስባቦች……

🌙ከአላህ ጋ እውነተኛ መሆን!!

በንግግር, በተግባር, ወደ አላህ በሚደረገው ጥሪ, ወደ ሰለፎች በሚደረገው ኢንቲሳብ እና በአጠቃላይ ከአላህ እና ከባሮቹ ጋ በሚደረገው ግንኙነት እውነተኛ መሆን አለበት።

🌙ዕውቀት!!

አጠቃላይ የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች ዕውቀት ላይ የተደገፉ መሆን አለባቸው።

🌙ወንድማማችነት እና ትብብር!!

በመተጋገዝ, በመተባበር, በመመካከር እና በመደጋገፍ ዳዕዋ ይጠነክራል። የራስ መንገድ እየሰነጠቁ በመለያየትና በመገንጠል ዳዕዋ ሊጠነክርም ሊቀጥልም አይችልም።

🌙ወደ ዑለማዎች መመለስ!!

ይህ ዳዕዋ የሚመራው በፖለቲከኞች ወይም ሌላ አላማ በሚያራምዱ ሰዎች ሳይሆን የነብያት ወራሽ በሆኑ ዑለማዎች ነው። ስለሆነም ጉዳያችን ወደ እነርሱ ስንመልስ ነገራችን ይስተካከላል።

🌙መጥራት መለየት!!

ዳዕዋችን, አካሄዳችን ቁርኣን እና ሓዲስ በመከተል ከሌሎች እንደ ሚለየው ሁሉ: እኛም ከሌሎች ጥመት ወይም ጅህልና ላይ ካሉ ሰዎች መለየት አለብን።

🌙መዘያየር!!

በመራራቅና በመጠፋፋት ክፍተት እና ድክመት እንደ ሚፈጠረው: በተቃራኒው መዘያየርና መገናኘት ጥንካሬ ያመጣል።

🪑ከሸይኽ

አቡ ሱለይማን ሰልማን ሙሓደራ የተወሰደ

https://t.me/hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

Telegram: Contact @hamdquante

ይህ ቻናል ቁርኣን እና ሐዲስ መሰረት በማድረግ የመልካም ቀደምቶቻችን ፋና በመከተል ስለ እስልምናችን የምንማማርበት እና የምንመካከርበት ቻናል ነው። ✍እስልምና አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው‼ ?????? @hamdquante አስተያየትዎ ይበልጥ ይገነባናል ?? @hamdquante_bot??
Send as a message
Share on my page
Share in the group